አዲሱ የብር ኖት ምን ምልክት ጨመረ ምን ምልክት ቀነሰ?


ዛሬ ኢትዮጵያ መቀየሯን ያሳወቀችው የ 10፣50፣100 ብር ኖት በቀለም በምልክት ምን ጨመረ ምን ቀነሰ?

10 ብር
አምሰት ብር ላይ የነበረው ቡና ለቃሚው ሰው ወደ አስር ብር ፊት ገፅ መጥቶ አዲስ ከተጨመረው የግመል ምስል ጋር አንድ ላይ ሆኖ ከነባሩ ከአንበሳ ምልክት ጋር ሆኗል። ሰፌድ የምትሰፋው ሴት ተነስታለች። ከጀርባ የነበረው በትራክተር መሬቱን የሚያርሰው ገበሬ ተነስቶ የአንድነት ምልክት በሚያሳዩ በአራት የቤተሰብ አባላት ተተክቷል። የብሩ መልክ ቀለል ካለው የድሮውን ቡናማ መልክ ትቶ ወደ ድሮ መቶ ብር ቀለም አረንጓዴ እና ነጭ በያዘ ቀለም ተቀይራል።

50 ብር
ቀለሙ ከቢጫ ወደ ቀላ ወዳለ ቀለም ሲቀየር ። በፊት ለፊት ላይ የነበረው በበሬ የሚያርሰው ገበሬ ተነስቶ በትራክተር በሚያርስ ገበሬ ተቀይሯል። በጀርባው የነበሩት የፋሲል ግንብ ጭስ በሚያወጡ ፋብሪካዎች ተተክቷል።
100 ብር
ሁለት በሬ ጠምዶ የሚያርሰው ገበሬ በፋሲል ግንብና በአክሱም ሀውልት ሲተካ በጀርባ የነበሩት የአክሱም ሐውልት፣ ተመራማሪው ሰው እና የተክል ቅጠል በሀረር ግንብና በሶፉ ኡመር ዋሻ ተተክቷል። ቀለሙ ከአረንጓዴ ወደ ውሃ ሰማያዊነት ተቀይሯል።

አዲሱ 200 ብር
ፊቱ ላይ በአፏ ቅጠል የያዘች ነጭ እርግብ ስትታይ በጀርባው ዳገት የሚወጣ አንድ ዋልያ እንሰሳ ይታያል። የወይን ጠጅ መልክም ይዟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *