ቢጂአይ ኢትዮጵያ አዲሱን የቢጂአይ ኤክስፒ ፕሮግራሙን ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አስተዋወቀ


በዚህ ፕሮግራም ተመርጠው የሚታቀፉ ተማሪዎችም በስራ ልምምዳቸው ጊዜ ሙሉ ወጪአቸው ይሸፈናል።

“የቢጂአይ ኤክስፒ የስራ መለማመጃ መርሀግብሩን” ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አስተዋወቀ
ቢጂአይ ኢትዮጵያ እ.አ.አ ጥቅምት 20 ቀን 2020 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የቢጂአይ ኤክስፒ የልኽቀት መርሃግብርን በጋራ ለመዘርጋት የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙ የሚታወስ ነው። በዚሁ መሰረትም መጋቢት 11,2013 ስምምነቱን ወደ ተግባር ለመቀየር እንቅስቅሴ ጀምሯል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ጊቢ ፍላጎት ላላቸው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ስለ በጂአይ ኤክስፒ የስራ ልምምድ ምንነት እና በመርሃ ግብሩ ለመሳተፍ መሟላት ስለሚገባቸው ጉዳዮች ማብረርያ በመስጠት መርሃግብሩን ለተማሪዎች ይፋ አደረጓል።

የቢጂአይ እድገት እና ስፋት በፍጥነት እያደገ እና እየተለወጠ የሚሄድ በመሆኑ፣ ተቋሙ በየግዜው ከዚህ ፍጥነት እኩል የሚራመድበትን እና ተግዳሮቶቹን በአሸናፊነት የሚወጣባቸውን አዳዲስ አሰራሮች እና የአሰራር ስልቶች በመቀየስ በዘርፉ ግምባር ቀደም ሆኖ ወደፊት በመራመድ ላይ ይገኛል። ይህ የቢጂአይ አክስፒ የስራ ልምምድ መርሃግብር ከነዚህ ስልቶቹ አንዱና ተማሪዎች የወደፊት ህይወታቸውን ብሩህ የያደርጉበት፣ ራሳቸውን ለውጠው ሀገራቸውን ለመለወጥ የሚያስችላቸውን ልምድ የሚቀስሙበት መድረክ ነው። መርሃ ግብሩ ተለማማጅ ተማሪዎቹ በተቋሙ ውስጥ የወደፊት ኑባሬ ስራቸውን ግንባታ የሚጀምሩበት እድል የሚሰጣቸው ሲሆን፣ ከተቋሙ ስራ አመራር ጀምሮ በየደረጃው ካሉ ባለሙያዎች እና ሰራተኞች ጋር ቅርርብ የሚፈጥሩበት ሲሆን፣ ስራ ለማግኘት እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ብቃቶችን፣ በቡድን መስራት፣ ችግሮችን መፍታት፣ በሰራ ቦታ ውጤታማ የሆነ ግንኙነትን የማድረግን ልምድ ያካብቱበታል። ቢጅአይ ይህን መርሀግብር ሲያዘጋጅ ዛሬ ባለው የስራ ውድድር ንቁ እና ብቁ ሆኖ ለመቆየት እንደ አማራጭ ሳይሆን አስፈላጊ እንደሆነ በማመን ነው።
በዚህ መርሃ ግብር ቢጂአይ ኢትዮጵያ የተቋሙን እሴቶች የሚያከብሩ፣ የድርጅቱን የስራ ባህል፣ ዘርፈ ብዙ የንግድ እንቅስቃሴዎቹን በሚገባ የተረዱ፣ ከፍተኛ የመስራት እና የመለወጥ ፍላጎት ያላቸው፣ ለተቋሙ የሚሟገቱ እና ኩባንያውን የመምራት ሃላፊነትን የሚረከቡ ፣ መረከብም ብቻ ሳይሆን ሀላፊነታቸውንም በብቃት የሚወጡ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ወጣት ባለሙያዎችን እንደሚፈጥር ያምናል።
በዚህ የስራ ልምምድ መርሃ ግበር መሳተፍ የሚፈልጉ ተማሪዎች ተቋሙ በሚያስቀምጠው ቀነ ገደብ ውስጥ በፍላጎት የሚመዘገቡ ሲሆን፣ በተለያዩ ምዘናዎች ውስጥ ማለፍ ይጠበቅባቸዋል። ተማሪዎቹ በነዚህ ምዘናዎች ማለፋቸው በራስ የመተማመናቸውን ከፍ ያደርገዋል። በተለማማጅነታቸው ጊዜ ከሚመኟቸው ሙያ ዘርፎች ጋር የተዛመዱ እውነተኛ የሕይወት ልምዶችን እና የማወቅ ዕድሎችን ያገኛሉ። በእርግጠኝነት የወደፊት ኑባሬ ስራቸውን ለመወሰን ብቃትም ይኖራቸዋል።
የቢጂአይ ኢትዮጵያ የስራ ልምምድ መርሃ ግብር በየአመቱ በክረምት ለሁለት ወራት የሚካሄድ ሲሆን ከመጀመሪያ አመት ጀምሮ ለሶስት ወይም ለአራት አመታት ተማሪዎቹን የሚያሳትፍ ይሆናል።
በዚህ የልምምድ መርሃ ግብር ለመሳተፍ የሚመረጡ ተማሪዎች በተለማማጅነት በሚቆዩባቸው ወራቶች ከተቋሙ የገንዘብ ድጎማ ይደረግላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *