እየተባባሰ የመጣውን ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዘውን ሞት ምን ያክል አሳሳቢ አንደሆነ ለመረዳት ፊደል ፖሰት በቀጨኔ መካነ መቃብር ተገኝተቶ የቀጨኔ ዘላቂ ማረፊያ ሀላፊ አቶ መኮንን ከስኬ አናግሮ የሚከተለውን መልስ አግኝቷል;
ኮሮና አሳሳቢ መሆኑን እዚህ የመቃብር ስፍራ ተገኝተቶ መረዳት ይቻላል በቀን 12 ሰው የሚቀበርበት ግዜ አለ ።ከዚህ ውስጥ ስምንቱ በኮሮና የሞቱ ናቸው ።
ቤተሰባቸው ያልታወቀ ሰዎች እዚህ በባይተዋር መቃብር ይቀበራሉ ። በቀን 40 ሰዎች ድረስ በዚህ በባይተዋር መቃብር ሶስት ወይም አራት ሰዎች በሰሌን ይቀበራሉ። የባይተዋር መቃብር እየሞላብን ይገኛል ብለዋል።