በጉማይዴ ህዝብ ላይ አሰቃቂ ግድያ እና መፈናቀል ተፈፅሟል ተባለ

የጉማይዴ ህዝብ የሰላም ኮሚቴ ዛሬ በኢትዮጵያ ሆቴል ዛሬ በሰጠው መግለጫ እስከ 1988 ዓ.ም ወረዳ ጎማይዴ ወረዳ የነበረች ቢሆንም ከመጋቢት 2003ዓ.ም ጀምሮ ግን ጎማይዴን ያላከታተ በሰገን የዞን ከተማ ማዕከልነት ተቋቁሞ የነበረው የሰገን ህዝቦች ዞን ምክንያቱ ፍፁም ሳይታወቅ ህዝቡም ሳይወያይበት ፈርሶ ኮንሶ ዞን አንዲሆን ተደርጓል ብለዋል።
በዚህም ፍትህና መልካም አስተዳደር ለማግኘት 160 ኪሎ ሜትር ተጉዘን ቡርጂ ሶያማ ከተማ ለማዳኘት ተዳርገናል ሲል ገልፇል።

ይህንንም አሰራር ኢ- ፍትሀዊ ነው ህዝቡ በማለቱ ከ40,000 በላይ ኗሪዎች በግፍ ተፈናቅለዋል ፣ከ80 በላይ ንፁሀን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ፣ከ300 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ያለ ፍትህ ታስረዋል ፣ዘጠኝ ቀበሌዎች ማሳቸው ተዘርፎ የገበሬዎች ቤት ተቃጥሏል ብሏል ኮሚቴው።
ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ገዛኸኝ በቀለ አንዳሉት የወረዳ አንሁን ጥያቄ ለአስተዳደር ምቹ አንዲሆን አንጂ የብሔር ጥያቄ አንዳልሆነ ተናግረዋል።
” እኛ ኮንሶ፣አማረኛ ፣ኦሮመኛ ፣አማረኛ ተናጋሪ ነን ። 145,000 ህዝቦች በላይ ህዝብ የሚኖርበት በውህድ ማንነት የምናምን ህዝቦች ነን ።ነገር ግን ወረዳ ብንሆን በሁለት እና በሶስት ኪሎ ሜትር ማግኘት የመንግስት አገልግሎት ማግኘት እየቻልን 54 ኪሎ ሜትር ለምን አንጓዛለን በማለታችን ጥይት ባነገቡ ከኮንሶ በመጡ ሀይሎች ሰው ተገድሏል ፣መስማት ማትችል ሴት ተደፍራለች ፣ገበሬዎች ማሳቸውን ትተው ሄደዋል፣ቤተ እምነቶች ተዘርፈዋል ” ብለዋል።

መንግስት ህዝቡ ተረጋግቶ የሚኖርበትን ሁኔታ የወረዳ ጥያቄ ይመልስ በማለት ጠይቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *