በዘንድሮ አመት መንግስታዊ ያልሆኑ 91 ት/ ቤቶች በአዲስ አበባ ሲዘጉ 23 አዲስ ደግሞ ተከፍተዋል

ፊደል ፖስት ከአዲስ አበባ አጠቃላይ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ተቆጣጣሪ ባለስልጣን  ባገኘው መረጃ መሰረት አምና ተገምገምው ለትምህርት ማስተማር በቂ ነገር ባለሟሟላታቸው በዘንድሮ አመት 91 መንግስታዊ ያልሆኑ ት/ ቤቶችን የስራቸውን ፍቃድ ተሰርዟል።
ከነዚህ ውስጥ 55ቱ ቅድመ መደበኛ ፣32ቱ የመጀመርያ ደረጃ አንዲሁም ሶስቱ ሁለተኛ ደረጃ የመሰናዶ ት/ ቤቶች ናቸው።
አንዲሁም በዘንድሮ አመት በከተማዋ 23 አዲስ የግል ት/ቤቶች ሲከፈቱ 15ቱ ቅድመ መደበኛ ፣7ቱ የመጀመርያ አንዱ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ የመሰናዶ ት/ ቤት ነው።

65 ት/ ቤቶች ደግሞ ተገምግመው ለዚህ አመት በማስጠንቀቂያ የታለፉ ሲሆን የሚጠበቅባቸውን መስፈርት ካላሟሉ በቀጣይ አመት ወደ ማስተማር አይገቡም ተብሏል።

በአዲስ አበባ ከ1,700 በላይ የግል ት/ቤቶች ሲኖሩ ት/ቤቶቹ በቦታ ጥበት ምክንያት በቂ ላይበረሪ ፣ላብራቶሪ ፣የስፖርት መጫወቻ ሳይሟሉ ሲያስተምሩ ይስተዋላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *