የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ሰኞ የካቲት 30 ,2012 ዓ.ም አመሻሹ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኮሮና ቫይረስ አሳሳቢ ደረጀ ላይ በመድረሱ ታላቁ የእግር ኳስ ውድድርን ሴሪ አን ጨምሮ ምንም አይነት ስፓርታዊ ክንውን እንዳይከናወን አዘዋል።
እገዳው አስከ መጋቢት 24,2012 የሚቆይ ሲሆን የበሽታው ስርጭት በዚው ከቀጠለ የእገዳው ጊዜ ሊራዘም ይችላል።
ጣልያን በቫይረሱ ባለፉት 24 ሰአት ውስጥ ብቻ 97 ሰው ሲሞትባት በአጠቃላይ እሰከ አሁን 463 ሞት እንዲሁም 7,895 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘውባታል።
በሽታውንለ መከላከል “ቀይ ዞን” በማለት በከተሞቿ ላይ ጥብቅ ምርመራ እና የሰዎችን የእግር እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ቀንሳለች።
ኮንቴ እንዳሉት ” አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰናል ።ለሀገራችን ጣልያን ስንል የማንደሰትበትን ነገር ሁላ በሽታውን ለመከላከል እናረጋለን ።ህዝባችንን በአጭሩ ለማለት የምፈልገው “ከቤታቹ ቆዩ ” ለስራ ወይንም ሌላ አስገዳጅ ነገር ካልመጣ በቀር በመንገድ ፣በትራንስፖርት አትንቀሳቀሱ ።ነገሮች አስኪለወጡ መታገስ ነው ያለብን ።” በማለት በአፅኖዎ ተናግረዋል።
የጣልያን ሴሪ አ 26 ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ባሳለፍነው እሁድ ጁቬንቱስና ከ ኢንተርሚላን ጨዋታን ጨምሮ በዝግ ስታዲዮም አንበሎች ዳኛን ሳይጨብጡ፣ ተቃራኒ ተጫዋቾችም ጨዋታ ሲጀምሩ ሳይጨባበጡ ነው ጨዋታው የተካሄደው።