በኢትዮጵያ በኩል የሚመጡ ሞተሮች ፣መኪኖች ድንበሯን አልፈው እንዳይገቡ ኬንያ በሞያሌ በኩል ያለውን የተሽከርካሪ ማለፊያን ፖሊሶቿን ይዛ መጥታ ትናንት እሮብ በእስካቫተር እንዳስቆፈረች የሞያሌ ነዋሪዎች ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።
እንደነዋሪዎቹ ገለፃ ቁፋሮው ዋና አላማ ምን አልባት በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ወይንም ወደ ኬንያ እንዳይገባ ነው ።
ኬንያ ከኢትዮጵያ በምትዋሰነብት ሞያሌ ከተማ ድንበር ላይ አምስት መተላለፊያ አስፋልቶች ሲኖሩ አምስቱም መቆፈራቸውን እና የአንዱ ጉድጓድ የጎን እርዝመት ከ20 አስከ 25 ሜትር ሲደርስ ጥልቀቱም አንድ ሜትር እንደሚዘልቅ ነዋሪዎቹም ተናግረዋል።