በኢትዮጵያ ለዶሮ የሚሰጡ ክትባቶችን ጥራት የሚመረምር የግል ላብራቶሪ ተከፈተ

በኢትዮጵያ ለዶሮ የሚሰጡ ክትባቶችን ጥራት የሚመረምር የግል ላብራቶሪ ተከፈተ

በኢትዪጵያ ከዘጠኝ በላይ ሰፊ የዶሮ ማርቢያ ያለው ኤጂፒ ፖልትሪ ቺክን የተባለ አሜሪካኖች በሽርክነት የሚመሩት ድርጅት ለዶሮ የሚሰጡ ክትባቶቸን ጥራቱን የሚመረምር ላብራቶሪ በመሀል አዲስ አበባ መክፈቱን አሳውቋል።

ላብራቶሪው በሀገሪቱ የዶር በሽታ በወረርሽኝ መልክ ሲከሰት የበሽታውን ምንነት የሚመረምር ሲሆን አንዲሁም ዶሮዎች የሚጥሉት እንቁላል በቁጥር ሲያንስ ያነሰበትን ምክንያት ናሙና በመውሰድ ምርምር ያከናውናል ተብሏል።

ላብራቶሪው ከግዜው ኤጂፒ ፖልትሪ ቺክን ሰር ላሉት ዶሮ ማርቢያዎች አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ለወደፊት ለሌሎችም ዶሮ ማርቢያ ድርጅቶች አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።
ኤጂፒ ፖልትሪ ቺክን ኢትዮ ቺክን በሚባል የምርት መለያ ስም ዶሮዎችን እያረባ እንቁላል ጨምሮ የሚሸጥ ሲሆን አምና ብቻ ወደ 23 ሚልየን ጫጩቶችን ፈልፈሎ ለሀገር ውስጥ ገበያ አሰራጭቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *