በኢትዪጵያ አየር መንገድ በአቶ ተሊላ ዴሬሳ የሚመራው የሰራተኛ ማህበር ሰራተኛውን ወክሎ ከየትኛወም አካል ጋር አንዳይደራደር በፍርድ ቤት ታገደ

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርም አቶ ተሊላ ለሚመሩት የሰራተኛ ማህበር የ50+1 እውቅና ሰርተክፌት ያለበቂ መረጃ ሰጥቷል በሚል ክስ ቀረቦበታል።

በካፒቴን የሺዋስ ፈንታሁን የሚመራው የኢትዪጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ለቂርቆስ ምድብ 2ኛ ፍትሀብሔር ችሎት ባስገባው ክስ ወረቀት መሰረት ፤ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ተሊላ ዴሬሳ ለሚመሩት ለቀዳማዊ የአየር መንገድ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር የ50+1 ወይንም የአየር መንገዱ ከግማሽ በላይ ሰራተኛ በአባልነት እንደያዘ በማድረግ የእውቅና ሰርትክፌት ያለ በቂ መረጃ ሰጥቷል በዚህም የአየር መንገድ ግሩፕ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበሩን ጉድቶታል በሚል ክስ ቀርቦበታል።

ፍረድ ቤቱም ቀዳማዊ ሰራተኛ ማህበሩ ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥ ድረስ ሰራተኛውን ወክሎ ከየትኛውም አካል ጋር አንዳይደራደር አግዷል።

ለታህሳስ 15,2013 በጉዳዩ ላይ የክርክር መልስ ለመስማት ቀጠሮ ይዟል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ መሰረታዊ እና ቀዳማዊ የሚባሉ ሁለት የሰራተኛ ማህበር ሲኖሩ በዚህ ጉዳይ ከሳሽ ሆኖ የቀረበው መሰረታዊው ማህበር በአግባቡ ተደራጅቼ እንዳልሰራ በአየር መንገዱ አስተዳደር በደል ይደርስብኛል የሚል አቤቱታ በተደጋጋሚ ጊዜ ማንሳቱ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *