በአዲስ አበባ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ቁጥር ለማወቅ ጥናት ሊደረግ ነው

ፊደል ፖሰት ከአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ያገኘው መረጃ አንደሚያስረዳው የኮተቤ ሜትሮፖሊቲያን ዩንቨርሰቲ በአዲስ አበባ የሚገኙ ጎደና ተዳዳሪዎችን ቁጥር ለማወቅ ለቢሮው የአራት ሚልየን ብር በጀት ያቀረበ ሲሆን በጀቱ ሲፀድቅለት ጥናቱ ይጀመራል ተብሏል።

ጥናቱ በጎዳና ተዳዳሪዎ ላይ ለሚሰሩ የመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጥሩ ግብአት ይሆናልም ተብሏል።
በአዲስ አበባ በሚኖሩ የጎዳና ተዳዳሪ ላይ ቁጥርን በተመለከተ የቅርብ ጥናት የተሰራ የሌለ ሲሆን ከ15 አመት በፊት የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፉ የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ያጠናው ሪፖርት አንደሚያመላክተው በከተማዋ ጥናቱ በተሰራበት ወቅት 89,000 ጎዳና ተዳዳሪዎች አንዳሉ ያመላክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *