“ቆሜ ልመርቅሽ” የድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ አልበም ከዳግማዊ ትንሳኤ በኋላ ይለቀቃል

ኢትዮጵያን “ቆሜ ልመርቅሽ” ያለበት የድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ የሙዚቃ አልበም ከዳግማዊ ትንሳኤ በኋላ ይለቀቃል ተባለ።

አልበሙ ሀገራዊና የፍቅር መልእክቶች የያዘ ሲሆን ከሞተ በኋላ አልበሙ ሊለቅ ታስቦ ግጥሞቹ በግዜው የነበረውን መንግስት ስለሚዳፈሩ ተፈርቶ ዘፈኑ ሳይለቀቅ አንደቆየ ተነግሯል።

የዛሬ 12 አመት በሞት የተለየው ድማፃዊ ጥላሁን ገሠሠ ከ 15 አመት በፊት ዘፍኗቸው ለህዝብ ያልተሰሙ 10 ሙዚቃዎች
“ቆሜ ልመርቅሽ” በተሰኘ የአልበም ስም ከዳግማዊ ትንሳኤ በኋላ እንደሚለቀቅ ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልፇል።
ለሙዚቃዎቹ መሰብሰብ ባለሀብቱ ሼክ አላሙዲ አስተዋፆ ከፍተኛ እንደነበረ የተነገረ ሲሆኑ ሙዚቃዎቹ አበጋዝ አፈወርቅ እንዳቀናበራቸው ተጠቅሷል። ሰባቱን ሙዚቆች ያየራድ አላምረው የገጠማቸው ሲሆን ዜማው ሞገስ ተካ እንደሰራው ተገልፇል።

ከፋሲካ በአል በኋላም የዝከረ ጥላሁን ገሠሠ የሙዚቃ ኮንሰርት አንደሚኖር የተነገረ ሲሆን ጥላሁን ገሠሠ የሚከበርበትና የሚወደሰበት የእራት ምሽት የሚዘጋጅ ሲሆን በዚህ ምሽት እያንዳንዳቸው አስር ሰው የሚይዙ እና በአንድ ሚልየን ብር የሚሸጡ 300 ጠረጴዛዎች እንደተዘጋጁ የተገለፀ ሲሆን ገቢውም ” ከገበታ ለሀገር ” መርሃገብር አንደሚውል ተገልፇል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *