ቃጠሎ ለደረሰበት ሞጣው መስጅድ 91 ሚልየን ብር በላይ ተሰብስቧል



የሞጣው መስጅድ ታህሳስ 10,2012 መቃጠሉን ተከትሎ ቤተ እምነቱን ለማደስ ትናንት ጥር 22 በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ 91 ሚልየን ብር መገኘቱን ትናንት ማምሻውን ኡስታዝ አቡበከር በፌስ ቡክ ገፁ አስታውቋል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በሌሎች 8 የግል ባንኮች በተከፈቱ የሒሳብ ቁጥሮች በርካታ የእስልምና ተከታዮች በሚልየን የሚቆጠር ብር አስገብተዋል። ጁማው አርብ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ በርሜል እስኪሞላ ብዙ ገንዘብ ተሰብስቦበታል። ክርስቲያኖችም “ከጎናቹ ነን” በማለት ለመስጅዱ ማደሻ ብር ሲያስገቡ ተስተውለዋል። የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ሙሉ ደሞዛቸውን የሰጡ ሲሆን እስክንድር ነጋ ፣ የዘመን ድራማ ተዋናዮች፣ ባንኮች፣የግለሰብ ድርጅቶች፣ሼኮች፣ ቄሶችም ተሳትፈውበታል ።ገቢ ማሰባሰቢያው አሁንም አንደቀጠለ ብሮችም እየገቡ ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *