ሚስተር ባምቢስ አረፉ!

“ልቤን ብትከፍቱት ኢትዮጵያዊ ነኝ” –

በአገሪቱ የመጀመሪያው ሱፐር ማርኬት እ.ኤ.አ. በ1931 የተከፈተው በአዲስ አበባ ፍትሕ ሚኒስቴር አካባቢ የተተከለው ሱፐር ማርኬት ነው፡፡

የዚህ ሱፐር ማርኬት መከፈት ለአካባቢው ባምቢስ የሚለውን መጠሪያም አጋብቶበታል ።

ባምቢስ የሱፐርማርኬቱ ይዞታም ቻራ ላምቦስ ሲማስ በተባሉ ግሪካዊ ባለሀብት ሥር ነበር፡፡
ግሪካዊው ሚስተር ባምቢስ ቺማስ ከአገራቸው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በ1944 ዓ.ም ነው። ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ገና የ21 ዓመት አፍላ ወጣት ነበሩ ፡፡ ባምቢስ ሱፐር ማርኬትን ከከፈቱበት ጊዜ ጀምሮ አካባቢው በስማቸው መጠራቱ ደስታ እንደሚሰጣቸውና እሳቸው ካለፉም በኋላ፣ ስማቸው ለዘላለም ኢትዮጵያ ውስጥ መቀጠሉን ሲያስቡት ኩራት እንደሚሰማቸው ተናግረው ነበር፡፡

ሚስተር ባምቢስ፤ ከሱፐር ማርኬት ስራቸው ጎን ለጎን ኢትዮጵዊያንን ለማገዝ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሰርተዋለወ። ‹‹ሞት በኩላሊት ይብቃ››ለተሰኘው የኩላሊት ህሙማን ማህበር የ1 ሚሊዮን ብር ‹በሮተሪ ክለብ በኩል ለግሰዋል፡፡

ሰበታ ውስጥ ለአይነ ስውራን ህክምና የሚያገለግል በ5 ሚሊዮን 120 አልጋዎች ያሉትና ባለ ሶስት ፎቅ ሆስፒታል አሰርተዋል፡፡ 3 ትላልቅ አምቡላንሶችን ለሆስፒታል ለግሰዋል። ሁለቱን ለፖሊስ ሆስፒታል፣ አንዱን ደግሞ ለየካቲት ሆስፒታል አስረክበዋል፡፡

የኢትዮጵያው ወዳጅ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በትናንትናው ዕለት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *