በጥቁር ገበያው አንድ ዶላር በሁለት ወራት ውስጥ የዘጠኝ ብር ጭማሪ አሳይቷል ። አንድ ዶላር 55ብር ድረስ ዛሬ ተገዝቷል

ፊደል ፖሰት በደረሰው መረጃ መሰረት በሁለት ወር ልዩነት ውስጥ በጥቁር ገበያው የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ ከሰባት ብር በላይ ከፍ ያለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት
በጥቁር ገበያው አንድ ዶላር አስከ 55ብር እየተገዛ ነው ።

ዛሬ ባንኮች አንድ ዶላርን በ39.36እየገዙ ሲሆን በጥቁር ገበያውና በባንኮች መሀከል በአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ ከ 15 ብር በላይ ልዩነት እያሳየ ነው።
በኢትዮጵያ የገንዘብ ኖት ከተቀየረ በኋላ የዶላር ዋጋ እያሻቀበ የመጣ ሲሆን ከውጭ በሚመጡ እቃዎች ላይ ባለፉት አራት ውስጥ ከ 40 አስከ 80 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እየታየ ነው።

ለዶላር ዋጋ መጨመሩ በውል የተጠና ጥናት ባይኖርም ወደ በሀገሩቱ የነበረው ጦርነት ፣ኮሮናቫይረስ የአለም ኢኮኖሚ መዋዠቅ የሀገሪቱን የንግድ አንቅሳቃሴ በመጉዳት የዶላር አቅርቦትን የቀነሰ ሲሆን ከብር ኖቱ መቀየር ጋር ተያይዞ በህገወጥ መንገዱ ዶላርን ከገበያ ስብስቦ ሀብትን ወደ ዶላር የመቀየር ሁነቶች ለዶላር ዋጋ መጨመር እንደ መላ ምት በአንዳንድ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይቀመጣሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *