በኢትዮጵያዊው ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የሚመራው አለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስን ከጅምሩ ለማስቆም በቂ መረጃ አልሰጠም ፣ይሄ ቫይረስ ጉዳት አንደሚያስከትል የአሜሪካ ደህንነቶች አስቀድመው ቢናገሩም ሰሚ አላገኙም በማለት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሀገራቸው ለአለም ጤና ድርጅት የምታደርገውን ድጋፍ አንዳቆመችሚያዝያ 6,2012 ማክሰኞ ለሊት ሲኤን ኤንን ጨምሮ ሌሎች መገናኛ ብዙሀን ባስተላለፉት የቀጥታ ሰርጭት ላይ ተናግረዋል።
በዚህም ምክንያት ድርጅቱ ከአሜሪካ በአመት የሚያገኘው 500 ሚልየን ዶላር ይቀርበታል ማለት ነው።
” ቫይረሱ ሲከሰት የአለም ጤና ድርጅት ወደ ቻይና የሚደረግ ጉዞ አንኳን እንዳይቀር ሲከለክል ነበር ።እኛ የቻይና በበራን አቁመን የብዙህ ሰዎችን ሒወት በኮሮና ከመጠቃት አድነናል። ድርጅቱ ከቻይና ባገኘው የተሳሳተ መረጃ ቫይረሱ አለም ላይ አንዲሰራጭ አድርጓል ።ለዚህም ተጠያቂ መሆን አለበት ።እኛም ለጊዜው ለድርጅቱ የምንሰጠው ድጋፍ አቁመናል ።” በማለት ተናግረዋል።
አሜሪካ በቫይረሱ እስከአሁን ከ25,000 በላይ ዜጎችን በሞት አጥታለች።