ቶታል ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት አንዲያግዝ የ17 ሚሊየን ብር ድጋፍ ሊያደርግ ነው


ቶታል ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ 19 ወረርሽኝ) ለምታደርገው ስራ የ17 ሚልየን ብር ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን ገልፇል።

ቶታል ኢትዮጵያ ማኅበረሰባዊ ኃላፊነቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመዋጋት የሚያስችሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለመቅረጽ እና ለመተግበር የሚያስችሉ መሠረታዊ ነገሮችን ለማሟላት ጥረት እያረኩ ነውም ብሏል።

ከነዚህም መሀል እያንዳንዳቸው 500 ሚ. ሊ. የሆኑና 80% የአልኮል ይዘት ያላቸውን 100,000 የዕጅ ንጽሕና መጠበቂያዎች (ሳኒታይዘር) በማምረት 15,000,000 ብር የሚገመት ዋጋ ያላቸውን 80,000 ጠርሙሶች ለጤና እና ለትራንስፖርት ሚኒስቴር – የተቀሩት 20,000 የዕጅ ንጽሕና መጠበቂያዎች ደግሞ ለሠራተኞች፣ ለከባድ የጭነት መኪና ነዳጅ አጓጓዦች እንዲሁም አጋሮቻችን ይለገሳሉ ሲል አስታውቋል።
በተጨማሪም በቶታል ካርድ አማካኝነት እስከ አንድ ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር የሚገመት ነዳጅ ለአንቡላንሶች እና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሥር ለሚገኘው የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አገልግሎትሰጪ መኪኖች ይሰጣሉም ሲል ተናግሯል።

ሁለት መቶ ሺ ብር ዋጋ ያላቸው 10,000 የንጽሕና መጠበቂያ ሳሙናዎች ረዳት ለሌላቸው አረጋውያን፣
ለጎዳና ተዳዳሪዎች እና እንደ መቄዶንያ ላሉ የበጎ አድራጎት ተቋማት ለመለገስና አንዲሁም 15 የቶታል ኢትዮጵያ ጣብያዎች እና በሌሎች ልዩ ልዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች 150,000 ብር ዋጋ ያላቸውን የዕጅ መታጠቢያ መሣርያዎች በመግጠም ለማኅበረሰባዊ አገልግሎት እንደሚያውል ገልፇል።

የሰራተኞቹን ደህንነት በይበልጥ ለመጠበቅ የአፍ መሸፈኛ ጭንብሎች፣ የዕጅ ንጽሕና መጠበቂያዎች እና የሙቀት መለኪያ መሣርያዎችን ከውጭ ሀገራት ለማስመጣት ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *