ከ 1,000 ሰራተኛ በላይ ያለው እድሜ ጠገቡ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ፣የኢትዮጵያ ሬድዮን እና97.1 ኤፍ ኤምን ያቀፈው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፕሬሽን( ኢብኮ) የሰራተኞችን ትምህርት የስራ ልምድ እና የቅርብ አለቃ ግምገማ ውጤት መሰረት አድርጎ ሰራተኞቹን በአዲስ መልክ ስራ ማደላደሉን አስታውቋል።
ፊደል ፖስት በደረሰው መረጃ መሰረት በአዲሱ የስራ መደብ ቅሬታ ተስምቷቸው ከ 234 በላይ ሰራተኞች ቅሬታ በዚህ ሳምንት አስገብተዋል ።
ቅሬታ ያስገቡት ሰራተኞች በአንድ ዳይሬክቶሪት ስር ሳይሰሩ ከሌላ ዳይሪክተሬት ምንም የስራ ልምድ ሳይኖራቸው የተመደቡ አሉ ።ይሄ በሰራተኞች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል በተጨማሪም አዲሱ ምድባችን ዕውቀታችንን፣ ልምዳችንን እና አቅማችንን ያገናዘበ አይደለም ሲሉ ለፊደል ፖስት ገልፀዋል።
በኢቢሲ ከ400 በላይ የሚሆኑ ጋዜጠኞች ይገኛሉ ።ከቅሬታ አቅራቢዎች ውስጥም በርካታ ጋዜጠኞች ይገኙበታል።