ከጅግጅጋ ተፈናቅለው በሱልልታ የሚገኙ ዜጎች በውሀ እጦት ተቸግረናል አሉ



ከሁለት አመት በፊት ከኢትዮ ሱማሌ ክልል በነበረ ግጭት ተፈናቅለው በሱልልታ መጠለያ የሚገኙ ከሶስት ሺ በላይ ዜጎች ውሀ እጦት አንደተቸገሩ እና በዚህም ምክንያት ከንፅህና ጉድለት ጋር ተያይዞ ለሚመጣ በሽታ እየተጋለጡ መሆኑን አስረድተዋል።

ከዚህም ባሻገር በሽንት ቤታቸው ሞልቶ እየፈሰሰ አንደሚገኝ እና ሽታውም የሰው ጤና እየጎዳ መሆኑን ተናግረዋል።
መድሀኒቶች ማግኘት ከባድ አንደሆነባቸው ለፊደል ፖስት የገለፁ ሲሆን በአካባቢው የምግብ እርዳታ ከመቀበል ውጪ ስራ ማግኘት ብዙ ሰው አንደተቸገረ ገልፀዋል ።

ከነዋሪዎቹ አንዱ የሆነው ቶፊቅ ዳውድ ስላለው ችግር አንዲህ ያስረዳል ” ውሃ በቦቴ ነው የሚመጣው ። እሱ ያልመጣ ለት ሩቅ ቦታ ሄደን ውሃ ለመቅዳት እንገደዳለን ።ኮሮና በተስፋፋበት ዘመን ውሃ ከለሌ አደጋው የከፋ ነው የሚሆነው ።” ሲል ስጋቱን ገልፇል።


በጉዳዩ ላይ ለፊደል ፖስት ምላሽ የሰጡት የሱልልታ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ሰለሞን ” ቦታው ረግራጋማ ስለሆነ ሽንት ቤቱ ቶሎ ይሞላል ።የውሀ ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራንበት ነው ። ስራ አጥነትን በተመለከተ ለተወሰኑ ግለሰቦች ቦታ ሰጥተን ሱቅ ከፍተው እየሰሩ ነው ።የሚቀረን ብዙ ስራ ግን አለን” ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *