የፋናው ጋዜጠኛ ማስረሻ ፍቅሬ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ሆኗል


በፋና ብሮድካሰቲንግ ኤጀንሲ ከ9 አመት በላይ የሰራውና ከጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ( JICA) ጋር ኤጀንሲውን በሚመለከት ዶክመንተሪ አየሰራ የነበረው ጋዜጠኛ ማስረሻ ፍቅሬ ኤጂንሲው ውስጥ ኮሮና ቫይረስ ከነበረባቸው ጃፓናውያን ጋር ንክኪ አለው ተብሎ ስለተጠረጠረ የቫይረሱ ምርመራ በጤና ሚኒስቴር በኩል ተደርጎለት ነፃ መሆኑን የቅርብ አለቃው አቶ አዳም ታደሰ ለፊደል ፖስት ገልፇል።
ጋዜጠኛው በሙሉ ጤንነት ቤቱ እንደሚገኝም ተናግሯል።
” በሶሻል ሚዲያ የተወራው ነገር አሳፋሪ ነው ።ጋዜጠኛው ስለተጠረጠረ ተመረመረ ።ውጤቱም ነፃ ሆነ።ይሄን ሳያረጋግጡ የውሸት ወሬ ማሰራጨት እጅግ አሳፋሪ ተግባር ነው ” ሲል አቶ አዳም ተናግሯል።

One thought on “የፋናው ጋዜጠኛ ማስረሻ ፍቅሬ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ሆኗል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *