የአዲስ አበባ ቃሊቲ ገሙሩክ ኮሚሽን ቅዳሜ የካቲት 14,2012 ባስተላለፈው ውሳኔ የታሰሩትን መኪኖች ጨምሮ ለህዝብ አገልግሎት ስም ገብተው ለግል አገልግሎት የዋሉት መኪኖች በመጪው አንድ ወር ውስጥ ታርጋቸውን ወደ ኮድ 3 ወይም 1 ካልቀየሩ ህጋዊ እርምጃ እወስዳለው ብሏል። ይህም ማለት መኪኖቹ ታርጋቸውን ካልቀየሩ እንደ መኪናቸው አይነት ሆኖ ከ 700,000 አስከ አንድ ሚልየን ብር ታክስ ሊከፍሉ ይገደዳሉ ማለት ነው ።
ባለፈው ሳምንት መጀመርያ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ተይዘው በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የታሰሩትና በአዲሰ አበባ ፣በኦሮሚያ፣በአማራ እና በደቡብ ክልል በ2 ቁጥር ታርጋ መሀል ሸገር ላይ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት D4D ፣ዳማስ እና ዶልፊን መኪኖች ባለቤት የታሰሩት መኪኖቻቸው እንዲፈቱላቸው አራሱ የጉሙሩክ ኮሚሽን ያዘጋጀውን የግዴታ ውል ማመልከቻ አየፈረሙ እንደሚገኙ ለፊደል ፓስት ተናግረዋል።