ሸራተን፣ራዲሰንና ፣ኢሊሊን ጨምሮ 95 በላይ ሆቴሎች ኮከብ ደረጃቸው ዳግም ሊመዘን ነው



የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከአራት አመት በፊት መዝኖ ከአንድ እስከ አምስት ኮከብ ደረጃ የሰጣቸውን ሆቴሎች ዳግም እስከ ሰኔ 2012 ድረስ ለመመዘን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ፊደል ፓስት የደረሰው መረጃ ያሳያል ።
በዚህም መሰረት ከአራት አመት በፊት ተመዝነው ባለ አምስት ኮከብ ደረጃ የተሰጣቸው ሸራተን አዲስ ፣ራዲሰን ብሉ ፣ካፒታልና ኢሊሊ ሆቴሎችን እንዲሁም በአራት ኮከብ ደረጃ ያሉት እነ ሂልተን አዲስን ጨምሮ ከ95 በላይ ሆቴሎች ዳግም የኮከብ ደረጃ ምዘና ያከናውናሉ።
ምዘናው 12 መመዘኛ ፈተናዎች ሲኖሩት የፅዳት፣የመኪና ማቆሚያቸው ፣የመኝታ ቤት አገልግሎታቸው ፣የማድቤት አያያዛቸውና፣የምግብና መጠጥ አገልግሎታቸውና የሰራተኛ ደረጃቸው ከመመዘኛ ነጥቦቹ ውስጥ ይገኙበታል።

ዳግም ምዘናው በየሶስት አመቱ የሚደረግ ሲሆን ሀገሪቱ ላይ ባለው ፓለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት አምና ሳይደረግ ቀርቷል።
ሆቴሎቹ መመዘኛውን ካላሟሉ ከነበራቸው ደረጃም ይወርዳሉ ።የተሻለ ነጥብም ካመጡ ባሉበት ደረጃ ወይንም ከፍ ወዳለ ኮከብ ያድጋሉ።
በመመዘኛው 80 ነጥብ የሚያመጣ ባለ አምስት ኮከብ ሲሰጠው 70 ያገኘ ባለ አራት ፣60 ያገኘ ባለ ሶስት ፣ 50 ያገኘ ባለ ሁለት ኮከብ ይሰጠዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *