በ 8 ጥይት በፖሊስ ለተገደለችው ብሪኦና ቴይለር ቤተሰቦች 12 ሚልየን ዶላር ሊከፈል ነውበአሜሪካ በሎዊስቪሊ ኬንታኪ የ26 አመቷ የሆስፒታል ድንግተኛ ክፍል ቴክኒሻን አደንዛዥ እፅ አለ ብለው ባለፈው መጋቢት ወር መጀመርያ ላይ ፖሊሶች በእኩለ ለሊት ቤቷ በመግባት በስህተት በተኮሱባት 8 ጥይት ለሞተችው ብሪኦና ቴይለር ቤተሰቦች ፖሊስ ህግን በመተላለፉ 12 ሚልየን ዶላር ሊከፈላቸው እንደሆነ ኮርየር ጆርናል ጋዜጣ አስነብቧል።

ብሩ የሚከፈለው የሎዊስቪሊ ኬንታኪ ግዛት አስተዳደር ሲሆን ቤተሰቧቿ ፖሊስ ላይ በቸልተኝነት ፣በስህተት እና ከበቂ በላይ ሀይል በመጠቀም ብለው ልጃቸውን በስህተት የገደሉት ፖሊሶች ላይ የከፈቱትን ክስ በድርድር ለመፍታት እና የግዛቲቱም ፖሊስ ስነ ምግባር የሌላቸውን ፒሊሶች አባሮ ትልቅ ለውጥ እንዲያመጣ በማሰብ ነው ።

የ26 አመቷ ጥቁር አሜሪካዊ ብሪኦና ቴይለር በተገደለችበት ቀን ከጓደኛዋ ከኒት ዋከር ጋር በክፍሏ የነበረች ሲሆን አደንዛዥ እፅ በቤቷ ተደብቋል ብለው ሶስት ፖሊሶች ቤቷ ሲገቡ ከኒት ዋከር ሰርሳሪ ሌባዋች መስለውት 25 ጥይት የተኮሰ ሲሆን አንድ ፖሊስም በተኩስ ልውውጡ አቁስሎ ነበር ።
አስገራሚው ነገር ግን በቴይለር ቤት አንዳችም አደንዛዠ እፅ አለመገኘቱ ነው ።

ፖሊሶቹ በተኮሱባት 8 ጥይት አልጋ ላይ የነበረችው ብሪኦና ቴይለር መሞቷ ከተሰማ በኋላ የጥቁር መብት ተከራካሪዎች ጉዳዩን ከአለም በማሰማት ቤተሰቧቿ ክስ እንዲመሰርቱ አርገዋል ።

የብሪኦና ቴይለር ግድያም በአሜሪካ እየተስተዋለ ካለው የዘረኝነት ተግባር ጋር ተያይዞ አጀንዳ መሆኑ የሚታወስ ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *