ደቡብ አፍሪካ በኮሮናቫይረስ ለተጎዳው ኢኮኖሚዋ ለ6 ወር የሚቆይ 500 ቢልየን ራንድ በጀት አፀደቀች


የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ትናንት ማክሰኞ ምሽት አንደተናገሩት ሀገራቸው በኮሮናቫይረስ የተጎዳባትን ኢኮኖሚዋን ለመደገፍ ለመጪው ስድስት ወር የሚቆይ የ 500 ቢልየን ራንድ ወይም በኢትዮጵያ 850 ቢልየን ብር በጀት ማፅደቃቸውን ተናግረዋል ።

እንደሬዉተርስ ዘገባ ምንም ገቢ የሌላቸው ዜጎች ለመጪው ስድስት ወር በየወሩ 350 ራንድ ወይም 650 ብር ገደማ በየወሩ ይቀበላሉ። ለልጆች ፈንድ ደግሞ ተጨማሪ 300 ራንድ በየወሩ ለቤተሰቦቻቸው እስከ ሰኔ የሚሰጥ ሲሆን ገንዘቡ ከሀምሌ ጀምሮ እሰከሚቀጥለው አመት ጥቅምት ድረስ ደግሞ በየወሩ 500 ራንድ ይሆናል ብለዋል።
ሌሎች በዙህ ማእቀፍ ውስጥ የተካተቱ ሰዎች በየወሩ 250 ራንድ እንደሚሰጣቸው ተነግሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *