ከ 30, 000 በላይ ይጎብኙታል ተብሎ የሚጠበቀው ኤክስፖ የኮንስትራክሽን ፤የቤት ሻጮችና ገዢዎች፤ አንዲሁም ገንቢዎችና የተለያዩ ተቋማትን ለማገናኘትና ለማስተሳስር እድል የሚሰጥ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሚሊንየም አዳራሽ ይካሄዳል ተብሏል።
ከፊታችን መጋቢት 9 እስከ 12 በሚካሄደው ኤክስፖ 120 የቤት አልሚዎች እየገነቡት ያለው ቤት ያለበት ደረጃ ፣ የቤቶቹን ዋጋ ፣ ሊገነቡት ስላቀዱት ቤት ፣ ስለሚፈልጉት እቃ እና አገልግሎት ከኤክስፖ ተሳታፊዎችና ከጎብኚዎች ጋር መረጃና ልምድ ይለዋወጣሉ ተብሏል።
አርኪ ኮንስትራክሽን ሌቨነት ኦርጋናይዘር ያዘጋጁት ይሄ ኤክስፖ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆነ ተቋማት፤ ጥሪ የተደረገላቸው ታላላቅ ተጋባዥ እንግዶች፤ አንድ ላይ በማቀናጀት በከተማ አንዲሁም በሀገር ደረጃ ሊሰሩ በታሰቡ መዋቅሪዊ ቅንጅቶች ላይ ፤ ልማታዊ ግቦች ላይና ዲያስፖራ ተኮር የሆነ የሀገር ግንባታዎች አሻራ ይጥላል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።

የአርኪ ሆም ኢቨንት ማናጀር አቶ ዩሃንስ ግርማ እንደተናገሩት ” በከተማችን አዲስ አበባ ቤት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚሸጡ ቢኖሩም በተዛባ መረጃ ምክንያት ቤት ሽያጭ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው። ከዚህም ባሻገር የቤት ግንባታ ላይ ያሉ ተዋናዮች በቂ ትውውቅ አለመኖራቸው የሚፈልጉትን ዕቃና አገልግሎት ለማግኘት እንደሚቸገሩና የዚህ አይነቱ ኤክስፖ የዚህ አይነቱን ችግር ለመቅረፍ ጎልህ ድርሻ ይጫወታል ” ብለዋል።