” ሰብዓዊ መብት የሚጥሱ ሰዎችን ለህግ ሊቀርቡ ይገባል ” ዶ/ ር ዳንኤል ጣሰው

በኢትዮጵያ  ባሉ የሀይማኖት እና የፖለቲካ ግጭቶች ላይ  በሰው ላይ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈፅሙ ሰዎች   ለህግ ማቅረብ ላይ ክፍተት አለ ይሄ ሊስተካከል  ይገባል ሲሉ የዓለም ዓቀፍ የማነቃቀት አገልግሎት ኃላፊ ዶክተር ዳንኤል  ጣሰው ተናገሩ ።
ትናንት በስካይ ላይት  ሆቴል በነበረ የምክክር መድረክ ላይ እንደተናገሩት ” ሰው በአደባባይ የሚማቱና የሚገሉ ሰዎች  ለህግ ማይቀርቡ ከሆነ  ስርዐተ አልበኝነት በሀገሪቱ  እንዲስፋፋ ምክንያት ይሆናል” ብለዋል።
” ሰው ክቡር ነው። ምንም ዓይነት ልዩነቶች በመነጋገገር መፍታት ይቻላል። የአንዳችን ህመም ሌላኛችን ሊሰማን ይገባል።  “


” የመገናኛ ብዙሃን የሰብአዊና  የዲሞክራሲ መብት ረገጣን በማስመልከት በሚገባው ያክል እየሰሩ አይደለም ። ለህዝብ እስከቆሙ  ድረስ  ወገንተኝነት ሳይታይባቸው ሊሰሩ ይገባል” ብለዋል።


አክለውም  የሰብዓዊ መብቶችን በተመለከተ ሪፖርት በማቅረብ ረገድ መሻሻል አለ ሲሉ ገልፀዋል።
በመድረኩ ላይ የተሳተፉት  የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር  አቶ ጥበቡ በለጠ  በበኩላቸው  ሰሞኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን   በደል ደረሰብኝ ብላ ብትናገርም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ምንም ሽፋን አለመስጠታቸው  እጅግ የሚያስተዛዝብ  ነገር ነው ብለዋል።
” ለቤተክርስቲያኗ በዓል እየመጡ  ዜና ፕሮግራም ይሰራሉ።ቤተ ክርስቲያኗ በደል ደረሰብኝ ፣ ቤተ ክርስቲያኖቼ ተሰበሩ ፣ ካህኖቼና ምዕመኖቼ  ተገደሉ፣ ተደበደቡ  ብላ ምዕመኗን ጥቁር አስለብሳ  ፆመና ምሕላ ስታደርግ  ሁሉም የመንግስት ሚዲያዎችና አንዳንድ  የግል ሚዲያዎች እንዳላዩ ማለፋቸው  ህዝብን መናቅና የቆሙበትን አላማ መርሳት ነው” ብለዋል።

የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው ወቅታዊውን የሀገራችንን ጉዳይ በተመለከተ  የተለያዩ አካላት ባወጡት  መግለጫ ላይ ለመወያየት ነው።

  ውይይቱን ያዘጋጀው  ዓለም ዓቀፍ የማነቃቃት አገልግሎት ሲሆን ተመሳሳይ መድረኮችም እንደሚዘጋጁ ተገልፇል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *