መጪው ክረምት አዲሱ መንግስታችን ያሳውቀናል ወይስ ..?

በኢኮኖሚ መቀዛቀዝና በፀጥታ ስጋት ላይ ያለችው ኢትዮጵያ በነሀሴ 10, 2012 ሀገራዊ ምርጫ አድርጋ ለቀጣይ አምስት አመት የሚመራትን ፓርቲ ለመምረጥ ቀን አየቆጠረች ትገኛለች። ብልፅግና ምርጫው ማካሄድ ግድ ይላል ሲል የዶክተር አብይ መንግስት ገፋኝ የሚለው ህወሐት ወቅቱ ክረምት ስለሆነ ለመራጮች አስቸጋሪ ነው ብሏል። የልደቱ አያሌው ኢዴፓ ሰላም በሌለበት ምርጫ እብደት ነው ብሏል። የዶክተር ብርሀኑ ነጋው ኢዜማ ለመራጮች ምዝገባ የተሰጠው 13 ቀን ትንሽ ነው ብሎ ቅሬታውን ያሰማ ሲሆን አብን እና ኦነግ ደግሞ መንግስት ምርጫውን ለማካሄድ ሰላም በቅድሚያ ያረጋግጥልን ብለዋል። ያም ሆነ ይህ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የምትመራው ምርጫ ቦርድ ምርጫውን የማራዘም እቅድ ያለው አይመስልም። ቦርዱ 25,000 የምርጫ አስፈፃሚ 547 የምርጫ ጣቢያ ለማዘጋጀት የተጣበበ ጊዜ ነው ያለው፤ የአቅሙን ግን እየሞከረ ነው። ምርጫው በተስፋና በስጋት ተከቦ ቀዝቃዛውን ነሀሴን እየጠበቀ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *