ፕሬዝዳንት ፓል ካጋሚ በአዲስ አበባ አረፍ የሚሉበት ቤት ሊገነቡ ነው



የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፓል ካጋሚ አዲስ አበባ አዋሬ አካባቢ ባለ ወደ 7,000 ካሬ የሚጠጋ መሬት ላይ ዘመናዊ ቪላ ቤት ለመገንባት እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ለፊደል ፓስት ተናግረዋል ።
በኢትዮጵያ የሩዋንዳ ኢምባሲ አምባሳደርና የሩዋንዳ መንግስት ሰዎች ከባለፉት አንድ ወር ጀምሮ ቤቱ የሚሰራበት የመንግስት ግቢ ውስጥ በተደጋጋሚ እየመጡ እንደሆነ እና ግንባታውን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት እያረጉ መሆኑን ፊደል ፓስት ከአካባቢው ሰዎች የደረሳው መረጃ ያመለክታል ።
ግንባታው ሲጠናቅቅ ፓል ካጋሚ ለእረፍት ወይንም ለስራ ጉዳይ አዲስ አበባ ሲመጡ ያርፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።
በጉዳዮ ላይ ፊደል ፓስት ሩዋንዳ ኢምባሲን ብታናግርም የኢምባሲው ሰራተኞች ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ የወጡ እንደሆነና ጊዜው ሲደርስ በጉዳዩ ላይ ኢምባሲው ይፋ የሚያደርገው ነገር ይኖራል የሚል ምላሽ ተሰጥቷል።
ለፓል ካጋሚ ማረፍያ ቤት አዲስ አበባ ውሰጥ መስጠት የታሰበው በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጊዜ ነበር።
ከአፍሪካ መሪዎች የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ አዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ ማረፊያ ቤት እንዳላቸው ይታወቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *