ፈረንሳዊው ቢልየነር ኦሊቨሬ ዳሶልት በሂሊኮፕተር አደጋ ሒወታቸው አለፈ

ሊ ፓርዢያን ጋዜጣ አንደዘገበው በኤሮስፔስ እና በሶፍትዌር ንግድ ላይ የተሰማሩት የ69 አመቱ ፈረንሳዊው ቢልየነር ኦሊቨሬ ዳሶልት በቶኪስ ከተማ በምትገኘው በሰሜን ካልቫዶስ ይበሩበት የነበረው ሂሊኮፕተር ተከስክሶ ሒወታቸው እንዳለፈ ተነግሯል።

ኦሊቨሬ ዳሶልት መሞት ተከትሎ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በቲወተር ገፃቸው በፃፉት መልእክት ” ኦሊቨሬ ዳሶልት ሀገሩን የሚወድ ፣ሀገሩን የጠቀመ የኢሮስፔስ ቴክኖሎጂን ከፍ ያደረገ ሰው ነው ።ሞቱ ትልቅ ኪሳራ ነው ለሀገራችን ።ለቤተሰቡና ለወዳጆቹ መፅናናትን እመኛለው ” ሲሉ ሀዘናቸውን ገልፀዋል።
ኢሊኮፍተሩ በምን ምክንያት አንደተከሰከሰ እስከ አሁን የተገለፀ ነገር የለም ።የሂሊኮፕተሩ አብራሪም መሞቱ ተነግሯል።

ፎርብስ የኦሊቨሬ ዳሶልት ሀብት 7.3 ቢልየን ዶላር ይገመታል ሲል መዘገቡ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *