ጠ/ ሚ አብይ አህመድ በበአለ ሲመታቸው አፍሪካውያን በምእራብውያን የእጅ አዙር አገዛዝ ላይ የሚያምፅቡት ጊዜ ሩቅ እንዳልሆነ አሳይተዋል።
እንግሊዝ በእጅ አዙር ምታሽከርክራት ኬንያ መሪዋን አዲስ አበባ ልካ ” ኢትዮጵያ እናታችን ናት ። ኢትዮጵያ ስትታመም እኛም እንታመማለን ” ማለቷ ለምእራብውያኑ ምቾት የሚሰጥ አይደለም። ብዙ አፍሪካ ሀገራት ነጭን ተዋግቶ ማሸነፍ አይቻልም ሲሉ በተግባር ነጭ ወራሪን አዋርዳ ነፃነት ያስተማረች ኢትዮጵያን በስስት የሚያዯት ሀገር ናት።
ኡሁሩ ” ብቸኛዋ በቀኝ ያልተገዛች ሀገር ” በማለት ኢትዮጵያን ሲያወድስ አሁንም ድረስ የቀኝ ግዛት ጣጣ ለአፍሪካውያን ህመም እንደሆነ አመላካች ነው። እንግሊዝና አሜሪካ እንዲሁም ፈረንሳይ የፈለጉትን መንግስት በማውረድ እና በማውጣት አፍሪካን እየዘወሩ መሆኑ እሙን ነው።
ለዛም ይመስላል ጠ/ ሚሩ ” ኢትዮጵያዊነት አይበገሬነት ” መሆኑን እናሳያለን በማለት ምእራባውያንን በቅኔ ሸንቆጥ ማድረግ የፈለጉት ።
ጠ/ ሚ አብይ አህመድ አሁንም ድረስ የጎሳ ፖለቲካ እየፈተናቸው ሀገራቸውንም ጦርነት ውሰጥ እንደከተታት ቢያምኑም ” በኢትዮጵያ አንድነትና ጥቅም ላይ ግን አልደራደርም ” ሲሉ ተደጋጋሚ ጊዜ ተሰምተዋል ።
ለምእራብያውያኑ የሚደነገጥ ልብ ያላቸውም አይመስልም ። ካልመሰላቸው የምእራብውያን ሀላፊዎችን ላያገኙ ይችላሉ ። የባይደን አማካሪ ፊልትማን ፣ የUSAID ሀላፊዋ ሳማንታ ፓወርን ሀገራቸው ቢመጡም አላገኟቸውም። ሰባት የ.ተ.መ.ድ ሀላፊዎችን ከሀገር ውስጥ ማስወጣታቸው”እኔ በምመራት ሀገር ያሻቹን ማድረግ አትችሉም” የሚል መልእክት ያለው ይመስላል።
ጠ/ ሚሩ” ህውሃት ለኢትዮጵያ አንድነት የማይጠቅም ” በግልፅ ባይናገሩም ” ተላላኪ መንግስት ” ነበረ በማለት የወረፉት ሲሆን ከህውሃት ጋር ከመታረቅ ሀገሬ ብድርና እርዳታ እንዲሁም ማእቀብ ይጣልባት የሚል አቋም ያላቸው ሲሆን ይሄ ሀሳባቸው ህውሃትን ለሚቃወሙ ደስታ ለሚደግፉ ሰዎች ደግሞ ጥላቻን አትሮፎባቸዋል። ያም ሆነ ይህ ግን በብዙ ግጭትና ጦርነት ቢታጀቡም ጠ/ ሚሩ በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊነት እንዲያድግ ሰርተዋል ቢባል ማጋነን አይሆንም።
ፈረንሳይ እንደ ልብ ምታሽከርክራት ጅቡቲ በመስቀል አደባባይ መሪዋ ኦስማን ጊሌ ” ኢትዮጵያ ለዘላለለም ትኑር ” በማለት ሲናገር ለተመለከተ ሰው አሁንም ቢሆን አፍሪካን ነፃነት ያስተማረች ሀገር እንድትበተን እንድትፈርስ እንሻም የሚል መልእክት ያለው ይመስላል። ጠ/ ሚሩ የተሻለ ሀገር እንዲሰሩ የጅቡቲ ፍላጎት መሆኑም የጊሌ ንግግር አመላካች ነው።
ፈረንሳይ ወታደሮች ይውጡልኝ የምትለው ማሊ ምእራባዊያን ጥርስ ውስጥ የገቡትን አብይ አህመድ ሹመት ላይ መገኘቷ ” የእኔም ልብ እንደ ኢትዮጵያ ነው ” የእጅ አዙር ቀኝ አገዛዝ በቃኝ ያለች ይመስላል።
አፍሪካዊቷ ናይጀሪያ ምእራበውያን ከቁብ ያልቆጠሩትና ያልታዘቡትን ጠ/ ሚሩን በድጋሚ ጠ/ ሚር ያደረገ ምርጫን ” ዲሞክራሳዊ ” በማለት የአንድ ሀገር ምርጫን የግድ ዲሞክራሳዊ ለማድረግ አውሮፓና አሜሪካ መገኘት እንደሌለባቸው ለመረዳት መሀመድ ቡሀሪ ትናንት በመስቀል አደባባይ ያደረጉትን ንግግር መስማት ነው።
ቡሀሪ በኢትዮጵያ ድንበር መከበርና በአንድቷ በማመመን የፖለቲካ ሀይሎች ጠመንጃ አውርደው ችግራቸውን በጠረጴዛ ዙርያ እንዲፈቱ ያስተላለፉት መልእክት የታመመች ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን ስጋት እንጂ ጤና እንደማታመጣ በመረዳት ነው።
የጎሳ ፖለቲካ ትርምስ አሁንም ነቀርሳ የሆነባቸው ሱማሌና ደቡብ ሱዳን ” ኢትዮጵያን እንደግፋለን ” ማለታቸው በተለይ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪየር ” ታላቋ እናታችን ኢትዮጵያ እንደኛ እንድትታመስ አንፈልግም ” ማለታቸው የምእራብውያን ሴራ ይብቃ የሚል መልእክት ያለው ይመስላል።