ግብፅ ትልቅ አሸባሪ ያለችውን ሂሻም አሽማዊን በስቅላት ቀጥታለች


በግብፅ መንግስት ዘንድ ቀንደኛ ተፈላጊ የነበረውና አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ሒሻም አሽማዊ ከሁለት አመት እስር በኋላ ባለፈው እሮብ በስቅላት መሞቱን የሀገሪቱ ጦር ቃለ አቀባይ ታምር አል ሪፋይ በይፋዊ ፌስ ቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል።
ከሊቢያ ከሁለት አመት በፊት ተይዞ የመጣው ሂሻም አሽማዋይ” ፋርፋራ ” በተባለ የመንገድ ጥቃት ድንበራ ላይ የነበሩ 22 የፀጥታ አስከባሪ ፓሊሶችንና መግደሉ ይታወሳል። በሲናይ በረሀም በርካት የሽብር ጥቀቶችን ፈፅሞ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን ገሏል።
በቅፅል ስሙ አቡ ኡመር አል ሙሀጂር ተብሎ የሚጠራው የ 42 አመቱ አሽማዊ ከአልቃኢዳ ጋር የተገናኘ የሽብር መረብ እንደነበረው የሚነገረለት ሲሆን በግብፅ የጦር ሀይል ውስጥም ለ15 አመት ያክል በተለያዩ የወታደርነት ማእረጎች አገልግሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *