ጆይ የቆዳና ፀጉር ንቅለ ተከላ ክልኒክ መንግስት ይቅርታ ይጠይቀኝ አለ

ጆይ የቆዳና ፀጉር ንቅለ ተከላ ክሊኒክ ህጋዊ ሆኜ  በመንግስት  ህጋዊ እንዳልሆንን በመገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው ዜና ሀሰተኛ ነው አለ

ከወር  በፊት  የአዲስ አበባ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን  በኢትዮጵያ ማርሻና ሀሌ ሉያ የተባሉ ክሊኒኮች    ብቻ ህጋዊ ፀጉረ ንቅለ ተከላ እንደሚያካሄዱ መነገሩ ሀሰተኛ  ነው ጆይ የቆዳና ፀጉር ንቅለ ተከላ  ክሊኒክም  በመንግስት እውቅና የተሰጠው  አካል ነው  ሲል  ዛሬ በሰጠው መግለጫ  ክሊኒኪ አስታውቋል።
የክልኒኩ ስራ አስኪያጅ  አቶ አዲስ የዓይን እሸት  እንደተናገሩት  ባለስልጣን በሰጠው መግለጫ ስሜ  ከመጥፋቱ ባሻገር  ገበያችንን  እስከ 80 ከመቶ ቀንሶብናል  ብለዋል።
” ከቱርክ በመጡ የፀጉር ንቅለ ተከላ ባለሙያዎች ነው  ስራ እየሰራን የነበረነው ። ለዚያም  ፍቃድ አለን ። ህጋዊ እንዳልሆንን መቅረቡ አግባብ አይደለም ።መንግስት ይቅርታ ሊጠይቀን ይገባል” ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *