የድምፃዊ ዮሴፍ ገብሬ ንብረት የሆነውና የቴሌቭዥን ስርጭቱን ካቆመ አራት ቀን የሞላው ጄቲቪ “ስልክና የኢንተርኔት አይሰራም” በሚል ምክንያት 40 የሚሆኑ ሰራተኞቹ መሾለኪያ አካባቢ በሚገኘው የጣቢያው መስርያ ቤት አንዳይገቡ ዛሬ ጠዋት መከልከላቸውን ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።

ጣቢያው ከቢራ ማስታወቂያ መከልከል እና ሰሞኑ ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ በቀዘቀዘው የማስታወቂያ ገቢ ወደ ኪሳራ እያመራ መሆኑን ምንጮች ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።
በጉዳዩ ላይ ፊደል ፖስት የጣቢያውን ሀላፊዎች ለማናገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
ጣቢያው ከተቋቋመ አራት አመት የሞላው ሲሆን ሰፖንሰር ገበያው በዚው ከቀጠለ ጣቢያው ሊዘጋ የሚችለበት ሰፊ እድል ሊኖር ይችላል ሲሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የጣቢያው ሰራተኞች ተናግረዋል።