ጂ አይ ኢትዮጵያ (BGI Ethiopia) አዲሱን የፈረንጆች አመት አስመልክቶ አበይት እቅዶቹን ይፋ አደረገ

አቶ ገብረስላሴ ስፍር፥ የድርጅቱ ኮሜርሺያል ፒ አር ማናጀር ሜክሲኮ በመጊኘው ዋናው መስራቤት ጥሪ ለተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ገለፃ ያደረጉ ሲሆን፤ ድርጅቱ በሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ያለው የሰላም ሁኔታ ከፍተኛ የመሻሻል እምርታን እያሳየ በመምጣቱ ስራውን አቁሞ የነበረውና ንብረትነቱ የ ቢ ጂ አይ የሆነው የ ራያ ቢራ ፋብሪካ መላውን ሰራተኞቹን እና ወኪል ድርጅቶቹን ወደስራ በማንቀሳቀስ በጦርነቱ ወቅት የገጠሙትን እክሎች በማስተካከልና የጎደሉትንም ግብዓቶች በማሟላት በአዲስ መንፈስ ወደስራ ሊገባ መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያን በአለም አቀፉ የወይን ምርት ላይም የተሻለች ተፎካካሪ ሀገር ለማድረግም ድርጅቱ ቢ ጂ አይ በትጋት በመስራት ላይ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። አክለውም ለመላው ህብረተሰብ መልካም የገና በዓልን ተመኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *