ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከቻይና ጋር በኮቪዲ19 ዙርያ የተለዋወጡትን መረጃዋች እንዲያቀርቡ ተጠየቁ


ከሶስት ቀን በፊት የተፃፈውና የ20 የአሜሪካን ኮንግረስ አባላት ፊርማ ያረፈበት ደብዳቤ አንደሚያሳየው የአለም ጤና ድርጅት ሀላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከባለፈው ነሀሴ ጀምሮ ኮቪዲ19 ጨምሮ ህብረተሰብ ጤናን በተመለከተ ከቻይና ጋር የተለዋወጡትን ደብዳቤዎችና ሪፓርቶች ሌሎችንም መረጃዎች አንዲያቀርቡ የኮንግረስ አባላቱ ጠይቀዋል ።
ከታይዋን ጋርም በቫይረሱ ዙርያ የተፃፃፉትን ሪፖርቶቹንና ደብዳቤዎችንም እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል።



ዶ/ር ቴድሮስ ከተጠየቁት ሪፖርቶች መሀል በቻይና ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ የሞቱ ፣የተጠቁ ሰዎችን የሚያሳይ ሪፖርት ይገኝበታል።
የኮንግረስ አባላቱ በደብዳቤው እንዳሰፈሩት ቻይና በሽታውን አቅላ ስትመለከት የአለም ጤና ድርጅትም ተገቢውን ትኩርት ሳይሰጥ ቫይረሱ በአለም ተሰራጭቶ ብዙ ሰው ሊገል ችሏል ብለዋል።


በተጨማሪም የአለም ጤና ድርጅት በቻይና ሪፖርት ተንተርሶ ቫይረሱ ከሰው ሰው መተላለፉን የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ አላገኘሁም በማለት በጥር መጀመርያ ወር ላይ በቲዊተር ያሰፈረ ሲሆን “ወረርሽኝ” ብሎ የተናገረውም በ19 ሀገራት የ 1,000 ሰው ሞት እና 10,000 ሰው በቫይረሱ ከተጠቃ በኋላ ነው ብሎ ሲገልፅ ይሄም ቫይረሱ “ወረርሽኝ “አስቀድሞ እንዳይባል የቻይና ተፅእኖ ነበረበት ብሏል። በዚህ ወቅትም የቻይናን ሪፖርት በማመን ድርጅቱ ” ቻይና በሽታውን ለመቆጣጠር አስደናቂ ስራ ሰርታለች ” በማለት አሞካሽቷል ።
ከዚህ በተጨማሪም ታይዋን አስቀድማ ቫይረሱ ከሰው ሰው ይተላለፋል የሚል ሪፖርት ስታደርግ የአለም ጤና ደርጅት ችላ ብሏል ሲል ደብዳቤው ወንጅሏል።
ዶ/ር ቴድሮስ ከዚህ ቀደም ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሰጡት ምላሽ ” ኮሮናን ፖለቲካ ከማድረግ ይልቅ ተገቢውን ጥንቃቄ እና የህክምና ስራ መስራት ለሁላችንም ይበጃል ” ሲሉ ተደምጠዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *