ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በዘር ጭፍጨፋ ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል የሚል አቤቱታ ቀረበባቸው።ከሁለት አመት በፊት የኖቤል ሰላም ሽልማት እጩ የነበረው አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት እና አክቲቪስት ዳቪድ ስቴንማን የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩን
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎች በማንነታቸው እንዲገደሉና አንዲሰደዱ ይሰሩበት ከነበረው መንግስት ጋር ተባብረዋል ለዚህም ሊጠየቁ ይገባል የሚል አቤቱታ ለአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ማስገባቱን አርቲ ሚዲያ ዘግቧል።

” ዶክተር ቴድሮስ ኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን በነበሩበት ጊዜ የደህነንነት ተግባራት ላይ ሚና የነበራቸው ሲሆን ይሄም የሰዎች መገደል ፣መታሰርና መገረፍን ” ያጠቃልል ነበር ይላል ኢኮኖሚስቱ ለፍርድ ቤቱ ያስገባው አቤቱታ ።
” በህውሃት አባልነታቸውና በከፍተኛ የመንግስት ሀላፊነታቸውን ጉልበት አንዲኖራቸው ያገዛቸው ሲሆን በዚህ ሰዎች ያለ ክስ ሲታሰሩና ወደ እስር ቤት ሲታጎሩ የእሳቸው እጅ ነበረበት ” ይላል የኢኮኖሚስቱ አቤቱታ።


አቤቱታው ዶ/ር ቴድሮስ በጋራ ሲሰሩበት ከነበረ መንግስት ጋር ፈፅመዋል ይበል እንጂ በተናጥል ይሄን ወንጀል እዚህ ቦታ የሚል አቤቱታ አላቀረበባቸውም።

አቤቱታው ተቃባይነት ካገኘ ዶ/ር ቴድሮስ በስራ ላይ እያሉ በአለም ዓቀፉ የመጀመሪያው ፍርድ ቤት የቀረቡ የመጀሪያው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን ይሆናሉ።

ይሄ የሚሆነው ግን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ጠርቶ ያለመከሰስ መብታቸውን ካነሳ ብቻ ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት ረገጣ ከዚህ በፊት የቀረበባቸውን አቤቱታ ማጣጣላቸው ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *