ዶ / ርሀተም ሳዴክ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን እንድታቆም ማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ።

ዶ / ርሀተም ሳዴክ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን እንድታቆም ማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሱዳን አየር ክልል አንዳያልፍ እየወተወተ ይገኛል።

በግብፅ በሄልዋን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆነው ዶ / ር ሀተም ሳዴክ በአባይ ወንዝ ላይ ግብፅ አለቃ ናት በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ የሚገነባ ሀገር የግብፅን ይሉኝታ ማግኘት አለበት ብሎ የሚከራከር ሰው ነው።

ግብፃዊው ዶ / ር ሀተም ሳዴክ ሰሞኑን በኢጅፕት ዲይሊ ኒውስ ላይ በፃፈው ፅሁፍ “ኢትዮጵያ የግል ሀሳቧን ብቻ ነው እያስተናገደች ያለችው። ይኸው 14 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በክረምት ልትይዝ ነው ።ባለፈው ዓመት ከተከናወነው የመጀመሪያ ሙሌት በሦስት እጥፍ የሚመበልጥ “በማለት ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅን ልትጎዳ ነው በማለት ፅፏል።

“ሱዳን ኢትዮጵያን በግድቡ ላይ ያላትን አቋም አውቃ ግድቡ ሊያመጣባት የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ዝግጅት ላይ ነች ። ይሄ አግባብ አይደለም የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ በአዳራዳሪነት መግባት አለባቸው የአፍሪካ ህብረት ብቻውን በቂ አይደለም ” በማለት ምእራባዊያን በግድቡ ላይ አንዲያደራድሩ እየወተወተ ይገኛል ።
ዶክተሩ ግብፅ አስዋንን ስትገነባ ኢትዮጵያን አንዳላስፈቀደች አባይ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ግብፅና ሱዳንን ሲመግብ ኢትዮጵያ የበይ ተመልካች መሆኗን ለሀገሩ ህዝብ ተናግሮ አያውቅም ።
ይልቁንስ ኢትዮጵያ ግድቡን ግብፅን ሳትሰማ ግንባታውን ከቀጠለች ” ሱዳን የአየር ክልሏን ለኢትዮጵያ በመከልከል
ከ10 በላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን በማስተጓጎል ወደ መካከለኛው ምስራቅ ፣ ሰሜን አፍሪካ ፣ አውሮፓ ፣ እስያ እና አሜሪካ የሚካሄዱ በረራዎችን በማሰረዝ ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ መጉዳት በማለት ” ፀብ ጫሪ ፁህፍ የፃፈ ሲሆን አገሩ ግብፅም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ለኢትዮጵያ እያስጠነቀቀች ነው ብሏል።
ምሁሩ ግብፅና ሱዳን ስለሚያደርጉት ጫና አንጂ የአባይ ወንዝ መነሻ ኢትዮጵያን ማስከፋት ሀገሩን አዘቅት ውስጥ አንደሚከት ፣ኢትዮጵያ በውጭ ሀገር ጠላት ተሸንፋ አንደማታውቅ ከአባይ ወንዝ ግብፅ ያለስጋት ውሃ መጠቀም የምትችለው ከኢትዮጵያና ከሌሎች የወንዙ ተፋሰስ ሀገራት ጋር በሰላም መስራት ሲቻል መሆኑን አይፅፍም ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *