ደቡብ ሱዳን ለግብፅ የጦር ሰራዊት ማረፊያ የሚውል የግንባታ መሬት ለመስጠት መስማማቷ ተሰማደቡብ ሱዳን ለግብፅ የጦር ሰራዊት ማረፊያ የሆነ ቦታ አንዲገነባ በላይኛው ናይል ተፋሰስ በኩል ባለ ፓጋክ በተባለ የሀገሪቱ ምስራቅ ክፍል የሚገኝ መሬት ለግብፅ ለመስጠት መስማማቷን SSNN የተባለው የደቡብ ሱዳን ሚዲያ ከመከላከያ ሰዎች ሰምቻለው ብሎ ዘግቧል ።
ሚዲያው የመከላከያ ሰዎች ነገሩኝ ይበል እንጂ ትክክለኛ ምንጩንና በስም ጠቅሶ አልተናገረም።

ቦታው ከ250 በላይ ላይ ወታደራዊ ቡድኖችን የማስተናግድ አቅምም አለው ተብሏል።

ግብፅ ይሄንን የወታደር ማረፊያ ለወደፊት ኢትዮጵያን የህዳሴ ግድብ አንዳትሰራ ጥቃት ለመፈፀም ልትጠቀምበት ትችላለች የሚል ግምት መኖሩን የጠቀሰ ቢሆንም ከደቡብ ሱዳንም ሆነ ከግብፅ ጉዳዩን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ የለም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *