“ዩንቨርስቲ መግባት በራሱ ግብ አይደለም። ወደ ግባችን ለመድረስ መሳሪያ ነው እንጂ ” የክቡር ኮሎጅ ዲን አቶ ደሳለኝ መኩሪያ

ክቡር ኮሌጅ 12 ክፍል የጨረሱ ተማሪዎች ዩንቨርስቲ ከመግባታቸው በፊት ” ምን መማር አለባቸው ? በእውኑ ግባቸውን ያውቁታል? የስሜት ብልህነታቸው እንዴት ነው? የስራ ፈጠራ አመለካከታቸው እንዴት ነው ? ከኮምፒዩተር ሳይንስ እና ከኢንፎርሜሽንና ቴክኖሊጂ ጋር ያላቸው ትውውቅ ምን ይመስላል? ” በሚሉ ርዕሶች ላይ ለሶስት ሳምንት በአዲስ አበባ ከ 133 ት/ ቤቶች የተውጣጡ ከ አንድ ሺ አምስት መቶ በላይ የ 12 ክፍል ተማሪዎችን የክህሎትና የቴክኖሎጂ ስልጠና ሰጥቷል።

አቶ ደሳለኝ ባለፈው ሀሙስ በስልጠናው ማብቂያው ላይ እንደተናገሩት ” ባለፈው 18 አመታት በነበረን የስራ ቆይታ የተዳነው የሀይስኩል እና የዩነቨርስቲ ግንኙነት በኢትዮጵያ በጣም ደካማ ነው ። ተማሪዎች ምን መማር እንዳለባቸው? ዩንቨርስቲ ሲገቡ የሚያጋጥሟቸው ችግሮችን እንዴት መቋቋም እንዳለባቸው? ትምህርት ከጨረሱ በኋላ ስራ መፍጠር እንዴት እንዳለባቸው? ሀገር እንዴት ማገልገል እንዳለባቸው ስልጠና የሚሰጣቸው አካል ብዙም የለም ።”

” ለብዙዎች ዩንቨርስቲ መግባት እንደ ግብ ይታያል ። እሱ አይደለም ቁም ነገሩ ። ቁም ነገሩ እየተማርኩት ያለ ትምህርት ከግቤ ያደርሰኛል ወይ? የሚለውን መመለስ ነው ” ብለዋል።

ክቡር ኮሌጅ በሚልየን የሚቆጠር ብር በመመደብ አምናም ተመሳሳይ ስልጠና በነፃ ለ 12 ክፍል ተማሪዎች መስጠቱ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *