የ66 አመቷ ናይጀሪያዊ ኒጎዚ ኦኮንጆ የአለም ንግድ ድርጅትን አንዲመሩ ተመረጡ


164 ሀገራት በመረጣ የተካፈሉበትን ምርጫ አብላጫ ድምፅ በማግኘት የ66 አመቷ ናይጀሪያዊ ኒጎዚ ኦኮንጆ የአለም ንግድ ድርጅትን አንዲመሩ ዛሬ የተመረጡ ሲሆን አለም ኢኮኖሚ ላይ እና ጤና ላይ በስፋት እሰራለው ሲሉ ከተመረጡ በኋላ ተናግረዋል።
ዶናልድ ትረምፕ ኒጎዚ ኦኮንጆ ድምፅ ነፍገው ቢሆምም አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ግን ድምፅ ሰጥቷቸው ኒጎዚ ኦኮንጆ መመረጥ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።
ኒጎዚ ኦኮንጆ ከዚህ ቀደም የናይጀሪያ ፋይናንስ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በአለም ባንክ ውስጥም ሰርተዋል። በአጠቃላይ በፋይናንስ ሴክተሩ ዙርያ የ25 አመት የስራ ልምድ አላቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *