የፀሀይ ሪልስቴት ነዋሪዎች የዛሬ ሰባት አመት የገዛነው ቤት ካርታ አልተሰጠነም አሉ

በቻይናዊ ባለሀብት የተመሰረተው ፀሀይሪል ስቴት ነዋሪዎች ደርጅቱ የዛሬ ሰባት አመት የገዛነው ቤቶችን የሽንሻኖ ካርታ ባለመስጠቱ ስጋት ላይ ወድቀናል ሲሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የነዋሪዎቹ ማህበር ፀሀፊ አቶ ቴዎድሮስ ይልማ ድርጅቱ ካርታውን ከመሰጠት ይልቅ ማህበሩ አፍርሶ ለመብቱ አንዳይሟገት ወከባ እያደረገብን ነው ብለዋል።

ቡና ባንክም ለድርጅቱ በነዋሪዎቹ የጥቅል ካርታ ብድር እንዳበደረ ገልፀው ይሄን ጉዳይ ለማስተካከል ባንኩ እየሰራ መሆኑን አቶ ቴዎድሮስ ገልፀዋል።

ቤቶቹ ለሀራጅ ቀርው እንዳሳገዱ ገልፀው ድርጅቱ ቤቶቹን ሲገነባ ባስነገረው ማስታወቂያ የልጆች መጫወቻ ፣ዋና አና ሆቴል አንደሚያካትት የተናገረ ቢሆንም ይሄን ወደ ጎን በመተው 240 ቤቶችን የሚይዝ አፓርተምንት ያለ ነዋሪዎች ፍቃድ በመገንባት ላይ አንደሚገኝ ገልፇል።
የአዲሱ ቤት ግንባታ ቤት ገዝተው በገቡ ነዋሪዎች ላይ በቂ የፀሀይ ብርሀን አንዳይገኙ በቂ የመኪና ማቆሚያ አንዳይኖራቸው ያደርጋል ብለዋል።

በሬልስቴቱ ውስጥ 634 ቤቶች ሲገኙ ማህበሩ 306 ነዋሪዎችን ያቀፈ ነው።
ነዋሪዎቹ ቤቱን በካሬ ሜትር በ 1200 የአሜሪካ ዶላር መግዛታቸውን አስታውሰዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *