“የአዲስ አበባ ወንዞችን እንዳይበከሉ ግንዛቤ ላይ መሰራት አለበት ” በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሳደር

በአለም አቀፍ ደረጃ ሴፕተምበር 27 የሚከበረውን “የወንዝ ቀን” ን አስመልክቶ አዲስ መካኒሳ ብሔራዊ አልኮል ፍብሪካ ከሚገኝ አቃቂ ወንዝ ዳርቻን የማፅዳት ዘመቻ ባለፈው ቅዳሜ መስከረም 15,2013 ተከናውኗል።

የፅዳት ፕሮግራሙ ላይ በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ ኢምባሲ የውኃ ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ፣በንፁህ የመጠጥ ውሃ፣ በህክምናና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በስፋት በመንቀሳቀስ የሚታወቀው (አምሬፍ )፣ኢትዮጵያ፣ የኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት( ኢትዮጵያ ) ኤስ .ኤን. ቪ ፣VItens Evides International Ethiopia (VEI)፣ አዲስ አበባ ከተማ የአስተዳደር ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ ፣ ግሪን ሮትራክ ፣ ሮታሪ ዓለም አቀፍ ኢትዮጵያ ተሳትፈዋል።

በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሰደር ሄንክ ጃን ባከር ወንዞችን ከፋብሪካና ከቤት ውስጥ ከሚመጡ በካይ ኬሚካል ፍሳሽና ደረቀቅ ቆሻሻ ለመከላከል ለማህብረሰብ ሰፊ የግንዛቤ ትምህርት ሊሰጥ ይገባል ብለዋል ።
” ወንዝ የሚሰጠን ጥቅም ተነግሮ አያልቅም ።ለሰው ፣ለእንሰሳት እንዲሁም ለእፅዋት ብዙ ጥቅም ይሰጣል። አሳ ይመርትበታል ፣ ውሃ ይቀዳበታል ፣ ኤሌትሪክ ይመነጭበታል፣በጀልባ ይኬድበታል፣ ዳርቻው መዝናኛ ቦታ ተሰርቶበት ጥሩ መዝናኛ ስፍራ በመሆን ገቢ ያመነጫል።

” ወንዞች ከተበከሉ ግን ይሄ ሁሉ ጥቅም ይቀራል። በአዲስ አበባ ወንዞችን ከቆሻሻ ነገርና ከብክለት ለመከለከል የወንዞችን ጥቅም በማስረዳት የማህረሰቡ አስተሳሰብ ላይ መስራት ያስፈልጋል ። የሰዎች አስተሳሰብ ከተቀየረ ብዙ ለውጥ ማምጣት ይቻላል።”

” በሀገሬ ኔዘርላንድ የሰዎችን አስተሳሰብ በመለወጥ ወንዞችን እንዳይበክሉ በማድረግ ትልቅ ስራ ተሰርቷል ። ይሄን እዚህ ማድረግ ይቻላል ” ብለዋል።

አምባሳደሩ አክለው የሀገራቸው መንግስት በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ በወንዞች እና በውሃ አጠባበቅ ላይ በኢትዮጵያ ፕሮጀክት ቀርፆ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *