ጉዳዩን በቅርብ ከሚያውቁ ምንጮች ሰማሁት ብሎ ሮይተርስ እንደዘገበው ምክትላቸው ፔይቶን ኖፕፍ ቦታውን እንደሚረከቡ ይጠበቃል ብሏል።
ፌልትማንን የተኩት ሳተርፊልድ አስከአሁን በቦታው ላይ ስድስት ወር የሰሩ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ስራውን ይለቃሉ ተብሎ ግን አልተጠበቀም ነበር ።
በቦታው ላይ ቶሎ ቶሎ ሀላፊዎች መቀያየር የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ላይ የባይደን አስተዳደር እንደተፈተነ ያሳያል ሲሉ ፖለቲካ ተንተኞች ይገልፃሉ።
ሳተርፊልድ የፊታችን ረቡዕ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናትንም ያነጋግራሉ ተብሎም ሲጠበቅ ነበር ።