የፕላስቲክ ማምረቻ የግብዓት እጥረቱ ካልተቀረፈ የታሸገ ውሃ ከኢትየጵያ ገበያ ሊጠፋ ይችላል ተባለ
የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት በኢትዮጵያ ያሉ የፕላስቲክና ጎማ ፋብሪካዎችን የማምረት አቅማቸውን ከ40 % በታች የሆነ ሲሆን በዚህም ምክንያት ፕላሲትክን ለማምረት የግበአት አጥረት ተከስቷል።
የኢትዮጵያ ፕላስቲክ እና ጎማ አምራቾች ማህበር በ 100 ፋብሪካዎች ላይ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ደርሼበታለው ባለው መሰረት በውጭ ምንዛሬ ባመጣው የግብአት ግዢ ችግር በዘርፉ ላይ ካሉ ፋብሪካዎች 85% ቱ ከ40% ባነሰ አቅም እያመረቱ እንደሚገኙ ገልፇል።
በዘርፉ ከ 4,500 በላይ የሚገኙ ሲሆን በውጭ ምንዛሬ እጥረት ከ20 ፋብሪካዎች በላይ እንደተዘጉ የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ምንተስኖት ለማ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል ።
ሰሞኑን በሀገሪቱ የተፈጠረው የታሸገ ውሃ እጥረት ፕላስቲክን ለማምረት የሚያስፈልጉት እቃዎች ለማሰገባት ዶላር ማግኘት ስላልተቻለ ነው ብለዋል።
“ከፕላስቲክና እጥረት ጋር ተያይዞ የታሸጉ ውሃዎች ከገበያ ሊጠፉ ይችላሉ። ወደ ውጭ ሀገር አሽገን የምንልካቸው የግብርና ምርቶች ላይላኩ ይችላሉ ።የመኪና ጎማዎች ማምረቻዎችም በግብአት እጥረት በቂ ምርት ባለማምረታቸው ጎማዎች እየተወደዱ ይገኛሉ ። ይሄን ለመቅረፍ ከመንግስት ጋር እያወራን ነው ።በጎ ምላሽ አግኝተናል ። ” ሲሉ ተናግረዋል።