በዝምቧቤ በስደት ላይ የሚገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንትየ 83 አመቱ ኮሎኔል መንግሰቱ ኃይለማርያም በኮሮናቫይረስ ተይዘው በዝምቧቤ ዋና ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ ፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ በዝምቧቤ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተናፈሰ ሲሆን ፊደል ፖስት ይሄን ለማጣራት ለዝምቧቤ መንግስት ሚዲያ የሚሰራ ጋዜጠኛ ጋር ደውሎ ያገኘው ምላሽ ይሄን ይመስላል ;
” መንግስቱ በኮሮና ተይዞ በፅኑ ታሟል የሚል ወሬ በሰፊው እየተናፈሰ ነው ።የሀገሪቱ መንግስት እስከአሁን ስለ እውነታው ማስተባበያ አልሰጠም ” ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
የሶሰት ልጆች አባት የሆኑት ኢትዮጵያን ለ17 አመት የመሩት ኮሎኔል መንግስቱ ከሀገር ከወጡ 30 አመት የተቃረባቸው ሲሆን በዝምቧቤ የመንግስት የፀጥታ እና የደህንነት አማካሪ በመሆን ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል።