የምእራቡ ዓለም የክፋት ዓይን አዘርባጃን ለዴሞክራሲ ያላትን ቁርጠኝነት አያደበዝዘውም


በዛሬው ዕለት አዛርባጃን የድል ምርጫ እየተባለ እየተገለጸ የሚገኘውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በማካሄድ ታሪክ እየስራች ነው፡፡ ይህ ታሪካዊ ምርጫ አዛርባጃን እያንዳንዷን ኢንቸ ግዛቷን ከአርሜኒያ ህገወጥ ወረራ ነጻ ካወጣች በኋላ የሚደረግ ነው፡፡ ይህ ምርጫ ሃገሪቱ ለተያያዘችው የፅናትና የእድገት ጎዳና ወሳኝ የሆነ መሠረት ይጥላል፡፡
ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የተውጣጡ ታዛቢዎች እና የመገናኛ ብዙሃን ተወካዮች በአዘርባጃን እየተካሄደ ያለውን የምርጫ ሂደት እያደነቁ ይገኛሉ። በምርጫው ሂደት ላይ የታዩትን ፍትሃዊነትና ግልጽነት ከጠበቁት በላይ እንደሆነ እየተናገሩ ነው። በቅድመ ምርጫ ቅስቀሳዎች ላይ እና በአጠቃላይ የምርጫው ሂደቶች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት የተሰጠው ሲሆን አዛርባጃን ያሳየችው የዲሞክራሲ ሂደት ለሌሎችም ምሳሌ የሚሆን ነው እያሉ ነው። ሃገሪቱ ለዲሞክራሲ መርሆዎች መከበር እና መጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት በምርጫ ሂደት ላይ ሚዛን ለመሆን ብቁ እንደሆነች ነው እየተናገሩ ያሉት።
በምርጫው ዋዜማ ባሉት ቀናት ላይ ያካሄደውን ሰፊ የአዛርባጃንን የሶሾሎጂ ጥናት ያካሄደ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገ ኦራክል አድቫይዘሪ ግሩፕ የተባለ ድርጅት እንኳን ሳይቀር ለምርጫው አዎንታዊ ድጋፍ ሰጥቷል። ድርጅቱ ስለጥናቱ ውጤት ጋዜጠኞችን ሰብስቦ ያስረዳ ሲሆን ጥናቱን ማካሄድ ያስፈለገው አዛርባጃናውያን በምርጫው ላይ ያላቸውን ንቁ ተሳትፎ ለመገምገም ነው። የጥናቱ ውጤቶች ያሳዩት ደግሞ አዛርባጃናውያን በምርጫው ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሆነ ነው። አዛርባጃናውያን ሃገራቸው ያለችበትን የእድገት ጎዳና እንደሚገነዘቡ፣ አዛርባጃን በምትከተለው ትክክለኛ አቅጣጫ ወደፊት እየተራመደች እንደሆነ እምነት ያላቸው መሆናቸውን እንደገለጹ እንደሆነ ነው ጥናቱ እንደጠቆመ ነው ድርጅቱ የገለጸው።
ይህ ምርጫ በመላ አዛርባጃናውያን ዘንድ ተቀባይነት ያለው፣ ተሳትፎው ከፍ ያለ፣ እና ተስፋ የተጣለበት፣ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ታዛቢዎችና እውቅ ጋዜጠኞች በመልካም ጎኑ እየታዬ እና ተቀባይነት እያገኘ ያለ ቢሆንም አንዳንድ የምዕራባውያን ሚዲያዎች እና ቡድኖች ግን በምርጫው ላይ መሠረተ ቢስ የሆኑ አሉታዊ መልእክቶቹን እያሰራጩ እንደሆነ እየታዘብን ነው።

የዲሞክራሲ እሴቶችን እናከብራለን የሚሉት እነዚህ የምዕራባውያን ተቺዎች አዘርባጃን በምርጫ ሒደቷ ያሳየችውን ግልጽነት እና ፍትሃዊነት መቀበል ተስኗቸዋል። የአዘርባጃን ህዝብ ከፍተኛ ድጋፍ እና እምነት የጣለበትን ይህን ምርጫ ማጣጣል የቆሙበትን አመክንዮ አልባ የሆነ አቋም ከማጋለጥ ሌላ ምርጫው ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ግን እምብዛም ነው። እነዚህ አንዳንድ የምዕራባውያን ቡድኖች እንዲህ ዓይነቱን አፍራሽ መልእክት የሚያስተላልፉት ለእነሱ ፍላጎት ያላጎበደዱ ነጻ ሃገራትን ሲሆን የሚያካሂዱትን ዴሞክራሲያዊ እድገቶችን የሚሸመጥጥ ነው።


የአዘርባጃን የምርጫ በቦታው በመገኘትም ጭምር እየተከታተሉ ያሉ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ነፃ ታዛቢዎችን የምርጫውን ሂደት በከፍተኛ ደረጃ አድንቆት እየተመለከቱት ነው። የእነዚህ የተለያዩ ታዛቢዎች አዎንታዊ አስተያየት አዘርባጃን ለዲሞክራሲያዊ መርሆች እና ለምርጫ ታማኝነት ቁርጠኛ የሆነች ሀገር በመሆኗ ያላትን መልካም ስም ያጠናክራል።
የአንዳንድ የምዕራባውያን ሚዲያዎች አሉታዊ ወሬ ግን የራሳቸው ድብቅ አጀንዳዎች እንዳላቸው ያሳያል። በአሉታዊነት ላይ በማተኮር እና የአዘርባጃንን ስኬቶች በማጣጣል በሀገሪቱ እና በሕዝቦቿ ድምጽ የተገኘውን እድገት ለማበላሸት መሞከር የራሳቸውን ቂላቂልነትን ከማጋለጥ በዘለለ እንደ አዛርባጃን ያለ የራሱን የዲሞክራሲያዊ ልማት አቅጣጫ እየቀየሰ ባለውና በክልሉ ተጽእኖ እያመጣ ያለ ሃገር ላይ ግን ጫና ሊፈጥር አይችልም።
አዘርባጃን የዕድገት እና የጽናት ጉዞዋን ትቀጥላለች። ይህ ታሪካዊ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫም የሀገሪቱን ለፈተና የማይበገር መንፈስ ማሳያ ሆኖ ያገለግላል። የግዛት አንድነቷን በተሳካ ሁኔታ ወደነበረበት መመለስ የቻለችው አዛርባጃን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ካመጣችው አስደናቂ ለውጥ ጋር ተዳምሮ ሀገሪቱን በቀጠናው ግንባር ቀደም ሃይል እና በአለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ሚና ያላት ተዋናይ እንድትሆን አድርጓታል። ይህ ምርጫም የአዘርባጃንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በማነጽ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ሚና ያጠናክራል የሚያጠናክር ሲሆን ሌሎች ተመሳሳይ ፈተናዎችን የተጋረጠባቸው ሃገራት በድፍረት እንዲጋፈጡ ያነሳሳል።
የዓለም አይኖች በጽናትና ቆራጥነት ወደ ፊት እየገሰገሰች ባለችው አዘርባጃን ላይ ትኩረት ያደረጉ ሲሆን በአንዳንድ የምእራባውያን ቡድኖች ዘንድ ያልተገባ አሉባልታ እየደረሰባት ያለችው አዛርባጃን ከጊዜ ወደ ጊዜ ተለዋዋጭ እየሆነ በመጣው የዓለም መድረክ ላይ የተስፋና የእድገት ምልክት ሆና መቀጠሏ አያጠራጥርም።
ዓለም አዛርባጃን ለተያያዘችው ወደ ብሩህ ተስፋ የሚያደርሳት አስደናቂእውቅና እየሰጠ ነው የምርጫው ሂደት እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት አዘርባጃን ዴሞክራሲያዊ እሴቶችን ለማስጠበቅ፣ መረጋጋትን ለመፍጠር እና የህዝቦቿን ቀጣይ እድገት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ቆማለች።
የመላው አዘርባጃናውያን ብርቱ ተስፋና እምነት እና የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች አድናቆት ከጥቂት የምዕራባውያን አሉባልታና መሠረተ ቢስ ጥርጣሬ የበለጠ ክብደት ያለው ሲሆን ይህም የአዘርባጃን ህዝብ የራሱን ዲሞክራሲያዊ እጣ ፈንታ ለመወሰን ያለውን ጽናት እና ቁርጠኝነት ያሳያል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *