የማዕድን ሚኒስቴር 116 የማዕድን ምርመራ ፍቃዶችን መሰረዙን አስታወቀ።

ፍቃዳቸው የተሰረዘባቸው ኩባንያዎች የማዕድናት ፍለጋ ፍቃድ ወስደው ለረጅም ጊዜያት በገቡትና ውል መሰረት ወደ ተግባር ስላልገቡ ነው ፍቃድ የሰረዝኩት ብሏል ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ።

በውላቸው መሰረት ማዕድን ምርት ማቅረብ ያልቻሉ 6 ኩባንያዎችም ፍቃደቸው ተሰርዟል ተብሏል።

ከማዕድናት ወጪ ገበያ መገኘት የነበረበትን ሀገራዊ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ያሳጡ 850 የማዕድን ላኪ ፍቃድ መሰረዙም ተነግሯል።

ባለፉት 11 ወራት ከወርቅ ምርት 513.9 ሚልየን ዶላር ከውጭ ገበያ ተገኝቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *