የማላዊ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውድቅ ተደረገ ።በ150 ቀናት ውስጥ ሌላ ምርጫ ይካሄዳልትናንት ጥር 25 ,2012 ጠዋት በወታደራዊ መኪኖች ታጅበው ማላዊ ርእሰ መዲና ሊሊንግዊ በሚገኘው የህገ መንግስት ፍርድ ቤት የገቡት ዋናዳኛ ሂሊ ፓታኒ ባለፈው አመት ግንቦት ወር ላይ የተደረገውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ህግ መጣስ ታይቶበታል ብል ውድቅ አድረገውታል።
ዳኛው 500 ገፅ ያለውን ማስረጃ ለማንበብ ከ10 ሰዓት በላይ የፈጀባቸው ሲሆን ሶስት ወር የከረመውን የፍረድ ቤት ክርክር ዳግም ምርጫ በ150 ቀናት ውስጥ ይከናወን በማለት መዝገቡን ዘግተውታል።
” የትኛውም ምርጫ ህገወጥ ተግባር ያጋጥመዋል ይሄም ምርጫ ያጋጠመው ህግ መጣስና ማጭበርበር ምርጫው ተአማኒ እንዳይሆን አርጎታል ።ስለዚህ ዳግም ምርጫ ያስፈልገዋል ” ሲሉ ዋና ዳኛው ፍርድ ሰጥተዋል።
ምርጫ እስኪከናወንም ድረስ አሁን ያሉት ፕሬዝዳንት ፒተር ሙታሪካ በጊዚያዊነት ሀገሪቱን እንዲያስተዳድሩ አዘዋል።
በአራት ሬድዮ ጣቢያዎች ቀጥታ ሲዘገብ የነበረው የፍርድ ቤቱ ችሎት ፍርድ ከተሰማ በኋላ በርካታ ማላዊያን ደስታቸውን በአደበባይ ወጥተው ሲገልፁ ነበር።
የባለፈውን ምርጫ ፒተር ሙታሪካ 38% በማግኘት አሸናፊ የነበሩ ሲሆኑ ነገር ግን 35% ያገኙት ላዘሪየስ ቻኪዌራ እና 20% ያገኙት ሳውሎስ ቺሊማ በምርጫው ከተመዘገበው አምስት ሚልየን ህዝብ ውስጥ የ 1.2 ሚልየን መራጮች ውጤት ተጭበርብሯል ብለው የሀገሪቱን ምርጫ ቦርድ ከሰዋል።
ፍርድ ቤቱም በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የውሸት ሪፓርት እንደተላከ ያረጋገገጠ ሲሆን የከሳሾችን ወጪ ምርጫ ቦርዱ እንዲሸፍንም አዟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *