የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዋና ዳሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ስራቸውን ለቀቁ

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዋና ዳሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ስራቸውን መልቀቃቸውን ፊደል ፖሰት ከታማኝ ምንጮች አረጋግጧል ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፀ/ ቤትም የስራ የመልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ተቀብሏቸዋል።

ዶ/ር ኤባ ለምን ስራቸውን መልቀቅ አንደፈለጉ አስከአሁን የተገለፀ ነገር የለም።

ዶክተር ኤባ ኢንስቲትዩትን ከአራት አመት በላይ የመሩ ሲሆን ኮሌራ ፣የቺኩንጉንያ እና ሌሎች ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር በርከታ ስራዎችም ከመስራታቸው ባሻገር በኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ የመመርመሪያ ላብራቶሪዎች በብዛት ከውጭ አንዲመጡ ፣ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ አንዲያደርግ ሰፊ ስራ ሰርተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *