ዛይራይድ 50,000 ጓንቶችና የአፍ መሸፈኛዎችን በነፃ እያከፋፈለ ነው



የኮሮና ቫይረስ ሰርጭትን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲረዳ ዛይራይድ ሜትር ታክሲ 50,000 ጓንቶችንና የአፍ መሸፈኛ ጭንብሎችን አዲስ አበባ ላሉ ሹፌሮች ፣ለጎዳና ተዳዳሪዎች ፣ለጥበቃዎች ፣ለፅዳት ሰራተኛዎችና ትራፊኮች በነፃ አያከፋፈለ መሆኑን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ሀብታሙ ታደሰ ለፊደል ፖስት በስልክ ተናግሯል ።
ጭንብሎቹና ጓንቶቹ በዛይራይድ ሜትር ታክሲ አሽከርካሪዎች በኩል እየተሰራጨ መሆኑንም ገልፆዋል።
” ሁሉም ነገር ሚሰራው እኛ ጤነኛ ስንሆን ነው ። ኮሮናን ለመከላከል መንግስት ብቻ በቂ አይደለም ። እኛም መረባረብ አለብን ። ቫይረሱ ጥንቃቄና ንፅህናን ይፈልጋል ። ለምሳሌ መስርያ ቤት ስናመራ ከበር ጥበቃዎች በባዶ እጅቸው ፣የአፍ ጭንብል ሳይደርጉ ሲፈትሹን ታያለክ ይሄ ለቫይረሱ ሊያጋልጣቸው ይችላል። ስለዚህ የአፍ ጭንብልና ጓንት ቢያረጉ የተሻለ በቫይረሱ ያለመያዝ እድላቸው ያንሳል ።እጅን በሳሙና መታጠብ ጨምሮ ሌሎች የጤና ባለሙያዎች የመከሩን ምክር እንዳለ ሆኖ ” ሲል ተናግሯል።

ዛይራይድ ከ7,000 በላይ ሜትር ታክሲዎችን ጋር ቴክኖሎጂ በማቅረብ እየሰራ ያለ ደርጅት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *