ዘምዘም ባንክ ” አሊፍ ” በተባለ ቅርንጫፉ ስራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኢስላሚክ ባንክ ሆኗል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ተሾሙዶክተር ይናገር ደሴ ዛሬ በአሊፍ ቅርንጫፍ ተገኝተው ባንኩን ስራ አስጀምረዋል።

ብሔራዊ ባንክ ለኢስላሚክ ባንክ መቋቋም መስመር ከከፈተ በኋላ ስድስት አዲስ ባንኮች ስራ ከመጀመር እንቅስቃሴ ቢጀምሩም ዘምዘም ባንክ በኢትዮጵያ የኢስላሚክ ባንክን ስራ ያስጀመረ ሆኗል።

ባንኩ ወሎ ሰፈር በሚገኘው በአረበኛ የመጀመሪያ በሆነው ፊደል ” አሊፍ ” ተብሎ በተሰየመ ቅርንጫፉን ስራውን በይፋ ጀምሯል።
ባንኩ 871.9 ሚልየን ብር የተከፈለ ካፒታልና 1.7 ቢልየን ጥቅል ካፒታል አንዳለው ተነግሯል።

11,000 ሰውም የባንኩ አክሲዮን ገዝቷል።

ከወለድ ነፃ አገልግሎትና ሌሎች የኢስላሚክ ባንክ አገልግሎቶችን ለመስጠት ታቅዶ የተከፈተው ባንክ በአመት ውስጥ ከ50 በላይ ቅርንጫፎችን አቅዶ እየተንቀሳቀሰ አንደሚገኝ ለፊደል ፖስት ገልፇል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *